Tuesday, August 18, 2015

በቤንሻንጉል ጉሙዝ የተገደሉት ሰዎች ሊጨምር እንደሚችል ነዋሪዎች ተናገሩ

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአለፈው ምርጫ ጋር ተያይዞ ፣ የአካባቢው ህዝብ የስርዓቱ ደጋፊ አይደለም፣ በምርጫውም ለመሳተፍም ሆነ ከመንግስት ጎን ለመቆም ፍላጎት አላሳየም በሚል የበቀል እርምጃ እንደተወሰደባቸው የአካባቢው ተወላጆች፣ የልዩ ሃይል አባላት በወሰዱት የጭካኔ እርምጃ እስካሁን በመንጌ ወረዳ 11 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸው፣ ግጭቱ ወደ ዳቡስ አካባቢም የተዛመተ በመሆኑ የሟቾቹ ቁጥር ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።

በመንጌ ከተማ አካባቢ በነበረ የአርብ ቀን ገበያ ላይ በተወሰደው አሰቃቂ እርምጃ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በተለይም ወደ ሜዳ ኦዶ ከተማና ዳቡስ አካባቢ ወደ ሚገኙ መልስተናኛ ከተሞች በሸሹት ግለሰቦች ላይ እርምጃ ተወስዷል።
በአካባቢው አሁንም ውጥረት ሰፍኖ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ገልጸዋል። በአካባቢው የተቃዋሚ ፓርቲዎች በአለፈው ምርጫ እንዳይሰተፉ የተከለከሉ ሲሆን፣ ህዝቡም ይህን ተከትሎ በምርጫው ላለመሳተፍ አቋም ወስዶ ነበር።
ኢሳት ታጠቂዎች በወሰዱት እርምጃ 12 ሰዎች መገደላቸውን፣ ከሟቾቹ ውስጥ 5ቱ ህይወታቸው ያለፈው እስር ቤት ከተወሰዱ በኋላ በምግብ ተመርዘው መሆኑንና 56 ሰዎች በመንጌ ወረዳ በአሶሳ ሆስፒታል በህክምና ላይ መሆናቸውን እንዲሁም 54ቱ ሰዎች መታሰራቸውን፣ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄን በመጥቀስ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment