Tuesday, August 18, 2015

የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር በመካሄድ ላይ ነው

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው ድርድር፣ ፕ/ት ሳልቫኪርና ተቀናቃኛቸው ሪክ ማቻር ተገኝተዋል። የድርድሩ የመጨረሻው ቀን ዛሬ ሲሆን፣ ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች ፊርማቸውን የማያኖሩ ከሆነ ማእቀብ ይጠብቃቸዋል ተብሎአል።

የተለያዩ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ድርድሩን በተመለከተ የሚጋጩ መረጃዎችን እየለቀቁ ነው። የዩጋንዳው መሪ ዩዎሪ ሙሰቬኒ ድርድሩ ሳይጠናቅ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

No comments:

Post a Comment