Tuesday, August 18, 2015

አንድ ሻንጣ ሙሉ ፓውንድ የተሸከመ ወያኔለንደን ላይ በቁጥጥር ስር ዋለ

( ኢሳት ዜና)
ወደ 150 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር በሻንጣ ጠርቆ ለንደን የገባ የሀገራችን ዘራፊ የወያኔ ባልደረባ በእንግሊዝ ፖሊሶች ክትትል እጅ ከፈጅ ተያዘ።ከፍርድ ቤት ጋር በተያያዘ ለጊዜው ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቁ ምንጮች እንደገለጹት ፣ አንድ የህወሃት አባል 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ወደ ለንደን ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች ተይዟል። ግለሰቡ ፍርድ ቤት ቀርቦአል።
ዳኛው ” ይህን ያክል ገንዘብ እንዴት በሻንጣ ልትይዝ ቻልክ የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ፣ ግለሰቡ ” ገንዘቡ የመንግስት መሆኑንና ለመንግስት ስራ ለማዋል መያዙን” ገልጻል። ይሁን እንጅ ዳኛው ” ይህን ያክል ገንዘብ በሻንጣህ የያዝከው በአገራችሁ ባንክ ስለሌለ ነው እንዴ? ” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል። ግለሰቡ በዋስ የተፈታ ሲሆን፣ መስከረም ላይ በድጋሜ ይቀርባል።

No comments:

Post a Comment