Thursday, July 19, 2018

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 12/2010) ለእረፍት ተበትኖ የነበረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያካሂድ ተነገረ።
ምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባውን በነገው እለት የሚያካሂደው በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው ለነበሩ ሰዎች ምሕረት ለመስጠት በሚቀርብ ረቂቅቅ አዋጅ ላይ ለመምከር ነው ተብሏል።
ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው ረቂቅ አዋጅ እና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ፓርላማው በነገው ውሎው የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተለያዩ የወንጀል ድርጊት የተሳተፉ ሰዎች ምህረት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ያጸድቃል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተጓደሉ የስራ አመራር ቦርድ አባላትን ለመሾም የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።

No comments:

Post a Comment