Thursday, July 5, 2018

በመልካ ጀብዱ በተነሳ ብሄር ተኮር ግጭት ሰዎች ተጎዱ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ/ም) በድሬዳዋ ከተማ ዙሪያ በምትገኘው መልካ ጀብዱ ሰኔ 26 ቀን 2010 ዓም በኢሳ የሶማሊ ጎሳዎችና በጉርጉራ የኦሮሞ ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት አንድ ሰው ሲገደል ፣በርካታ ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። ግጭቱን የድሬዳዋና የአካባቢውን ስልጣን ለመቆጣጠር ያለሙ የአካባቢው ባለስልጣናት እንዳስነሱት ነዋሪዎች ተናግረዋል። ግጭቱን ተከትሎ በተነሳው አመጽ አህመድ አብዱልሀኪም የሚባል ወጣት ተገድሏል። ሌሎች ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ደግሞ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። በሌላ በኩል በድሬዳዋ ፌደራል ማረሚያ ቤት ውስጥ ታስረው የሚገኙ እስረኞች በግቢው ውስጥ ስላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ታውቋል። እስረኞቹ ባደረጉት ሰልፍ፣ የድሬዳዋ ማረሚያ ቤት አሰተዳዳሪ መኮንን ደለሳ፣ የጥበቃ ደህንነት ዘርፍ አስተባባሪ ገ/ስላሴ ስብሃቱ፣ የተሃድሶ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ ሃይሉ ለገሰ እንዲሁም የፋይናንስ ዘርፍ አስተባባሪ ጋሻው ድሪባ ከስልጣን እንዲነሱላቸው ጠይቀዋል።

No comments:

Post a Comment