Saturday, July 21, 2018

ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከአገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከብሄራዊ መረጃና ደህነት፣ ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር ሆኖ ህብርተሰቡን ማዕከል ባደረገ መልኩ በተከሄደው የጥቂት ቀናት ዘመቻ ገንዘቡ ከአገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ጥቂት ቀናት በጥናት ላይ ተመርኩዞ በተካሄደው ዘመቻ ከ1ሺህ በላይ የነፍስ ወከፍና የቡድን ጦር መሳሪያ እንዲሁም 80 ሺህ የሽጉጥና ክላሽ ጥይቶች ወደ አገር ሊገቡ ሲል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽ ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡
ከገንዘቡ በተጨማሪ በህገ ወጥ ድርጊቱ ላይ የተሳፉ ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገባቸው መሆኑንም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከአገር ሊወጣ ሲል፣ የጦር መሳሪያው ደግሞ ወደ አገር ሊገባ ሲል መያዙ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጫና ለመፍጠርና አገራዊ አለመረጋጋትን ለመፍጠር ያለመ የተቀናጀ ስራ መኖሩን ተገንዝቦ ፖሊስ ጥልቅ ምርመራ እያረገ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡
ህብረተሰቡ የአገሪቱን ኢኮኖሚና ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አሁንም ከፖሊስ ጎን ሆኖ የተለመደ ትብብር ማድረጉን እንዲቀጥልም ኮሚሽነር ዘይኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከዚህ በኋላም በተመሳሳይ መልኩ በጥናት ላይ የተመሰረተ እርምጃ መወሰድ እንደሚቀጥልም ተመልክቷል፡፡
ሪፖርተር፡ ጥላሁን ካሳ

No comments:

Post a Comment