Thursday, July 5, 2018

ሰሞኑን በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለሱዳኑ ፕሬዚዳንት መልዕክት መላካቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዘገበ።

(ኢሳት ዜና ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰሞኑን በሁለቱ ሀገራት በሚዋሰኑባቸው የድንበር አካባቢዎች ግጭት ተቀስቅሶ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች መሞታቸውና በርካቶች መጎዳታቸው ይታወቃል። የሱዳን ታጣቂዎች ድንበር አሳብረው በመግባት ” የእርሻ መሬት ይገባኛል” በሚል በፈጸሙት ጥቃት የተቀሰቀሰው ግጭት በሚቆምበት እና በሀገራቱ ድንበሮች አካባቢ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን መሥራት በሚያስፈልግበት ሁኔታ ከዶክተር አብይ-ለሱዳኑ አቻቸው የተላከውን መልዕክት ያደረሱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነ ገበየኹ ናቸው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መል ዕክቱን ባደረሱበት ወቅት ከፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ጋር ሰሞኑን በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ በተስተዋለው የፀጥታ ችግር ዙሪያ መወያዬታችውን የሱዳን ትሪቢዩን ዘገባ ያመለክታል። ፕሬዚዳንት አልበሽርም በድንበር የሚከሰቱትን ችግሮች ሁለቱንም ሀገራት በማይጎዳ መልኩ ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል መግፍባታቸው ተመልክቷል። እንደ ጋዜጣው ዘገባ፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርሩ ከዚህም ባሻገር ከሱዳኑ አቻቸው ከኤል ዲልደሪ ሞሃመድ አህመድ ጋር ተገናኝተው በተመሣሳይ የጸጥታ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

No comments:

Post a Comment