Friday, July 6, 2018

አሜሪካና ቻይና የንግድ ጦርነት ውስጥ እየገቡ ነው

 (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) የትራምፕ አስተዳደር ቻይና ወደ አሜሪካ በምትልካቸው እቃዎች ላይ እስከ 25 በመቶ የሚደርስ የቀረጥ ጭማሪ ማድረጉን ተከትሎ ፣ ቻይናና ሩስያ ተመሳሳይ እርምጃዎችን ወስደዋል። ቻይና በአለማችን የተከሰተ ታላቁ የኢኮኖሚ ጦርነት ስትል የአሜሪካንን ውሳኔ አደገኝነት ገልጻለች። አሜሪካ 34 ቢሊዮን ዶላር በሚደርስ የቻይና ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ ጭማሪ ስታደርግ፣ ቻይናም እንዲሁ ተመሳሳይ እርምጃ ወስዳለች። ሩስያም የቻይናን ፈለግ በመከተል ከአሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የቀረጥ ጭማሪ አድርጋለች። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከአውሮፓ፣ ሜክሲኮና ካናዳ በሚገቡ የብረትና አሉሚኒየም ምርቶችም ላይ ተመሳሳይ የቀረጥ ጭማሪ አድርገዋል።

No comments:

Post a Comment