
ወደ ኢቲቪ ቢሮ በመሄድ ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። እንዲሁ በርካታ የመዲናቅዋ ወጣቶች ኢንጂነሩ ሞተው በተገኙበት በመስቀል አደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በጎንደር ከተማም እንዲሁ ሞቱ ያስደነገጣቸው ወጣቶች ወደ አደባባይ በመውጣት ቁጣቸውን ገልፀዋል። ኢንጂነሩ ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ስራውን በበላይነት በመቆጣጠር ግድቡ አሁን ላለበት ደረጃ አድርሰውታል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ሞት እንደሰሙ መደንገጣቸውንና ሀዘናቸውን መግለጻቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል። እንደ ኃላፊው አቶ ፍጹም አረጋ ገለጻ ዶክተር አብይ ይህን አስደንጋጭና ልብ ሰባረኢ ዜና የሰሙት አሜሪካ ሲደርሱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ለኢንጂነር ስመኘው በቀለ ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማስተላለፋቸውንም ከአቶ ፍጹም ገለጻ ለመረዳት ተችሽሏል።
No comments:
Post a Comment