Sunday, July 8, 2018

ራያ አላማጣ እየታመሰች ትገኛለች

Image may contain: one or more people and outdoorImage may contain: one or more people and outdoor1. በርካታ ቁጥር ያላቸው የክልሉ ልየ ሃይል፣ ፖሊስና በርካታ ቅጥር ያላቸው ምሊሻዎች በከተማዋ ሰፍረው ህዝቡን እያሸበሩት ይገኛሉ
2. ከ4፡300 ጀምሮ እንደ ጎርፍ የጎረፈው ሰላማዊ የአላማጣ ነዋሪ ሰድድ እሳት እያቀጣጠሉበት ይገኛሉ
3. በዚህም ሁለት ወጣት ልጆች ክፉኛ ተጎድተው ይባስ ብለው ፖሊስ ጣብያ ወስደው እየደበደቧቸው ይገኛሉ
4. በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች በኦራል ተጭነው ወደ ፖሊስ ጣብያ አጥር ግቢ ከወሰዷቸው በኋላ እደበደቧቸውና ግፍ እየተፈፀነባቸው ይገኛል
5. ኮተት የሌለው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ይዘው የተገኙ ወጣቶች እንዲደበደቡና ባንዲራቸዉም ተጠቀምተው እንዲቀደድባቸውና ሁለት ባንዲራ አቃጥለውባቸዋል
6. አሁን ተጨማሪ ልዩ ሃይል ከወደ መቀሌ እየዘመመ ይገኛል
7. ባስቸኳይ ከዋጃ ጥሙጋ ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸው የነበሩት የክልሉ ልዩ ሃይል ከቦታው ለቆ መውጣት ባለመቻሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃዉሞቸውን እያሰሙ ይገኛሉ
8. ዋጃ ጥሙጋ ሶስት ቦታ ላይ መንገድ ዝግ ሆኗል
9. ኮረም ወጣቶ ለተቃዉሞ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል
10. የዶር አብያ ፎቶ ያለበት ቲሸርት የለበሱ 7 የራያ አላማጣ ወጣቶች ታፍነው ተወስደዋል

No comments:

Post a Comment