Thursday, July 19, 2018

ባለስልጣናት ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 12/2010)ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እና ለኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስኪያጅ መሾማቸው ተነገረ።
ከሁለቱ መስሪያቤቶች የተነሱት የቀድሞ የስራ ሃላፊዎች ደግሞ በሌላ ቦታ ተመድበዋል።
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት የቀድሞው የአዲስ አበባ መንገዶች ባልስልጣናት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝ ናቸው።
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አርዓያ ግርማይ ደግሞ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸው ነው የተገለጸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት ዶ/ር አንዷለም አድማሱ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል።
በምትካቸውም የተቋሙ ምክትል ስራ አስፈጻሚ የነበሩት ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ ተተክተዋል። ዶ/ር አንዷለም አድማሱ በትምህርት ሚንስቴር የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው ተነግሯል።
በኢትዮ ቴሌኮም ዋና የኦፕሬሽን ሓላፊ የነበሩት አቶ ኢሳያስ ዳኘው ተነስተውም በምትካቸው የቴክኖሎጂ ኦፊሰር የነበሩት አቶ አማረ አሰፋ መተካታቸውን በሐገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

No comments:

Post a Comment