Tuesday, July 10, 2018

ኢትዮጵያና ኤርትራ ታሪካቸውን መቀየራቸውን ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ

Image may contain: 1 person, smiling( ኢሳት ዜና ሃምሌ 3 ቀን 2010 ዓ/ም ) ጠ/ሚኒስትሩ ለኤርትራው ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ በጻፉት ደብዳቤ ፣ ሁለቱ አገራት መራርና አውዳሜ ጊዜ ማሳለፋቸውን ጠቅሰዋል። አሁን ያ የታሪክ ምዕራፍ ተዘግቶ ሁለቱ አገራት አዲስ የሰላም ግንኙነት መጀመራቸውም ጠ/ሚኒስተሩ ገልጸዋል። በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ኢትዮጵያ ዝግጁ ናት ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፣ በኤርትራ በነበረው ቆይታቸው ከመንግስት ባለስልጣናትና ህዝቡ የተደረገላቸውን መስተንግዶ አድንቀዋል። ኢትዮጰያ እና ኤርትራ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ብዙዎችን አስገርሟል።

No comments:

Post a Comment