Monday, July 23, 2018

ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ እንዲመጡ ከስምምነት ተደረሰ

Image may contain: 9 people, people standing(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረው የእርቅ ጉባኤ ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ እንዲመጡ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ።
በዚህም የቀድሞው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ የቤተክርስቲያኒቱን መንበር እንዲይዙ ይደረጋል ማለት ነው።
አሁን በሃገር ቤት ባለው ሲኖዶስ ያሉት አቡነ ማቲያስ ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱን የአስተዳደር ስራ እንዲሰሩ ተወስኗል ተብሏል።

ለሰላም ድርድሩ ተቀምጠው የነበሩት አባቶችም በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
የእርቅ ጉባኤው ከመካሄዱ በፊት አስቀድሞ የሁለቱም አባቶች የተገናኙበት የጋራ የጸሎት ስነስርአት ተካሂዶ አንደነበር ታውቋል።
የሐገር ቤት የመጡት አባቶች በውጪ ሲኖዶስ በሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት የጸሎት ስነስርአት ላይ ሲገኙ የውጪ ሲኖዶሱ አባላት ደግሞ በሐገር ቤቱ ሲኖዶስ በሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት ላይ ተሳታፊ መሆናቸው ተሰምቷል።

No comments:

Post a Comment