Thursday, March 24, 2016

በኢትዮጵያ የሚታየው ህዝባዊ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን አንድነት እያጠናከረ እንደሚመጣ ዶ/ር ዲማ ነገዎ ገለጹ

ኢሳት (መጋቢት 15 ፥ 2015)

በኦሮሚያ ክልል አራት ወራት የዘለቀው ህዝባዊ እንቅስቃሴ እንዲሁም በጎንደር፣ በኮንሶና፣ በሌሎች አካባቢዎች የተነሱ የህዝብ ንቅናቄዎች ህዝብን እያስተባበረና የኢትዮጵያን አንድነት እያጠናከረ እንደሚመጣ ዶ/ር ዲማ ነገዎ ገለጹ።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መስራችና የመጀመሪያው ሊቀመንበር የነበሩት ዶ/ር ዲማ ነገዎ፣ ይህንን የተናገሩት ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው።

ለስራ ጉዳይ ከሰሜን አፍሪካ ወደ ዋሽንግተን ብቅ ያሉት ዶ/ር ዲማ ነገዎ ለኢሳት በሰጡት በዚህ ቃለምልልስ፣ በኦሮሚያ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ከ1966ቱ አብዮት ወዲህ ያልታየ በማለት የገለጹ ሲሆን፣ በዚህ መጠን ገበሬዎችን ያሳተፉ እንቅስቃሴ በአለም ታሪክ አልተመዘገበም ሲሉ የህዝባዊውን እንቅስቃሴ ስፋት አሳይተዋል።
የኦሮሞ ህዝብ እንቅስቃሴ በጥቅል ለኢትዮጵያ ያለውንም ፋይዳ አመልከተው፣ የሌሎች ኢትዮጵያውያን ድጋፍም እንደሚያስፈልግ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (አዴግ) ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ዲማ ነገዎ ዛሬ በኦሮሚያ የቀጠለውና በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚታየው ህዝባዊ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን ጠንካራ አንድነት እንደሚያመጣም የራሳቸውን ዕምነት ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment