Tuesday, March 8, 2016

ለተቃውሞ የወጡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደበደቡ

የካቲት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ግድያ ይቁም የሚል መፈክር በመያዝና ነጭ ጨርቅ በማውለብለብ ወደ አሜሪካ ኢምባሲ ያመሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ፣ በአካባቢው ሲደርሱ በፖሊሶች ተደብድበዋል።

ተማሪዎቹ “እኛ አሸባሪዎች አይደለንም፣ ግድያው ይቁም!” የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል። ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን ተከትሎ ተማሪዎች ቢበታተኑም፣ ፖሊሶቹ ግን ተቃውሞውን አስተባብረዋል ያሉዋቸውን ይዘው በማሰር ላይ ናቸው።
በወለጋ ዩኒቨርስቲ ፖሊሶች በተማሪዎች መኝታ ከፍሎች ውስጥ ገብተው ባደረሱት ድብደባ በርካታ ተማሪዎች ተጎድተው ሆስፒታል መተኛታቸውም ታውቋል።

No comments:

Post a Comment