Wednesday, November 18, 2015

ትግርኛ ተናጋሪው VOA ጋዜጠኛ ወሎ ድረስ ምን ኣስኬደው?~~

ግርማይ ገብሩ ወይዘሮ ብርቱካን ለBBC የሰጡትን ቃለመጠይቅ ውሸት መሆኑን ለማረጋገጥ በፌደራል ህግ መሰረት ትግራይ ክልልን ተሻግሮ ኣማራ ክልል ድረስ ዘልቆ ወይዘሮ ብርቱካን ኣነጋግረዋል። ኣማራ ክልል ውስጥ ለምን ሄደ ?ማንስ ላከው? ትግራይ ክልል ውስጥ የሚጣራ ነገር ጠፍቶ ነው? ወይስ ሌላ ኣጀንዳ ኣለው? የሚለውን ማይቱ ሳይሻል ኣይቀርም፣

ከዛ በፊት ግን ግርማይ ገብሩ ይሕን ከመጻፉ በፊት እሁድ ጥዋት ገዛ ተጋሩ ፓልቶክ ሩም መጥቶ ምን ተናገረ? ግርማይ ገብሩ እሁድ እለታ ገዛ ተጋሩ ፓልቶክ ሩም መጥቶ ስለ መጽሃፉ፣ስለድርቁ፣ትግራይ ውስጥ ስላለው የትግርኛ ስነ ጽሁፍ ኣወራ፣ ውጭ ያሉትን የትግራይ ልጆች መጽሃፉን በመግዛት እና በመሸጥ እንደተባባሩትም ተናገረ፣ ግርማይ ገብሩ ኣንዲት የረሳት ነገር ግን ነበረች!!!! .
~~~ታሪኩ እንዲህ ነው፣ መቀሌ ውስጥ የተዘጋጀውን የትግራይ የዳያስፖራ ፌስቲቫል ላይ ግርማይ መጽሃፉን ሰማእታት ኣዳራሽ ውስጥ ለመሸጥ ሲሞክር ኣዳራሹን ለቆ እንዲወጣ በደህንነት ኣባል እንደተነገረው እና እሱ ካልወጣ ግን መጽሃፋቸውን ለመሸጥ የመጡ በሙሉ እንደሚያባርሩ ለሱ በግሉ ይነግሩታል(ይነገረዋል)፣ እሱም የደህንነት ኣባሉ ያለውን ተፈጻሚ ከማድረግ ሌላ ምርጫ እንደሌለው ስለሚያቅ ኣዲት መጽሃፍ ሳይሸጥ ኣዳራሹን ለቆ ወጣ፣ በተፈጸመበት ነገር ሁላችንም ኣዘንን!!!ግርማይ ገብሩ ገዛ ተጋሩ ፓልቶክ ሩም ላይ መጥቶ ይችን ቃል ኣልተናገረም፣ምክን ያቱ ደግሞ ገዛ ተጋሩ ፓልቶክ ሩም ውስጥ ህውሃትን መውቀስ ኣትችልም፣ እኛም ይህንን ሃቅ የሚያጣራ የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን። . .
~~~በዚህ ብቻ ኣላበቃም ግርማይ ገብሩ መጽሃፉን ለማስተዋወቅ መቀሌ ላይ በተደረገው ምርቃት የትግራይ ክልል ሬድዮ እና ቲቪ ጥሪ ቢደረግላቸውም ኣልመጡም፣ ያልመጡበት ምክን ያት ግርማይ ራሱ ሲናገር እንዲህ ይላል፣ ሁለት ጊዜ መጽሃፌን ሳስመርቅ ለትግራይ መገናኛ ቡዙሃን ጥሪ ባደርግም ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ኣልመጡም፣ ይህቺን ነገር ማን እንዳደረጋት ከላይ ወደታች ራሴን ኣጣርቼ ደርሼበታለሁኝ ይላል፣እኛ ግን ማን እንደሆነ እስካሁን ግርማይ ራሱ ኣልነገረንም። የትግራይ ክልል ፕረዚዳንት ናቸው ወይስ የደህንነት ሃላፊዎች፣ይቀጥላል ግርማይ “እኔ በታገልኩለት እህት ወንድሞቼ በታገሉለት በተሰዉለት መብቴ በትግራይ ኣለመከበሩ ኣዝናለሁኝ ይላል”። በነገራችን ላይ ግርማይ ገብሩ የህውሃት ታጋይ ነበር። ለታጋይም መብት የሌላት ትግራይ እያለች ነው ወሎ ድረስ ሄዶ የውሸት የጋዜጠኝነቱን መብት ያከበረው።እኛም ይህንን ሃቅ የሚያጣራ የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን። .
~~~እኔም እሁድ እለታ” ግርማይ ገብሩን የማያቅ የትግራይ ልጅ ቢያጋጥማቹ ብየ” በትግርኛ የጻፍኩት ያላንዳች ምክንያት ኣልነበረን። ፓልቶክ ሩም ውስጥ ግርማይ ገብሩ እንግዳ ሆኖ ሲመጣ ማን መሆኑን የማታቅ ኣድሚን ስለነበረች ነው፣ ኣስቡት እንግዲህ ስለትግራይ እቆሮቆራለሁኝ የምትል የህውሃት ደጋፊ ግርማይ ገብሩን ያወቀችው ያሁኑ እሁድ ነው ኣጃይብ ነው ኣለ ያጌሬ ሰው። ግርማይ ገብሩ ስለ ብርቱካን ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረው ገዛ ተጋሩ ሩም ውስጥ ነው፣ እኔ ዛሬ ኣይደለሁም የሰማሁት እሁድ ጥዋት ነው እናም ኣይገርመኝም። .
~~ግርማይ ወሎ ድረስ ምን ኣስኬደው?ትግራይ ውስጥ ስንት የሚጣራ ውሸት እያለ ከክልል ወደ ክልል ምን ያስኬዳል፣ እስኪ ትግራይ ውስጥ ያሉት ውሸቶች ሊጣሩ የሚችሉትን እንይ፣ . . .
~~ሃይለማርያም ደሳለኝ የትግራይ ገበሬ 100% ዘመናዊ ኣርሶ ኣደር ሆኖዋል ይላሉ፣ ኣሁንግን የትግራይ ገበሬ ርሃብ ላይ ይገኛል ከክልል ወደ ክልል ከመሮጥ እዛው ያለበት ክልል ውስጥ ይህንን ማጣራት ኣይቻልም ነበር ወይ? . .
~~ትግራይ ውስጥ የውሃ ኣቅርቦት 92% መድረሱን የትግራይ ክልል ይናገራል!!!ነገር ግን ትግራይ ውስጥ ውሃ በሳምንት ኣንዴ እንካን ከመጣች እልል ነው፣ ይህንን ነገር ውሸት መሆኑን ኣለመሆኑን ለማጣራት ለምን ከበደው? ዞሮ ዞሮ ትግራይ ውስጥ ብዙ የሚጣራ የውሸት ዳታ የመልካም ኣስተዳደር ችግር እያለ ለምን ወሎ ድረስ ኣስኬደው? ፍራቻ!!! ከሙያ እና ከህሊና ይልቅ ለደሞዝ መኖርን ስለሚሻ።እኛም ይህንን ሃቅ የሚያጣራ የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን። . .
~~ሌላም ኣለ አቶ ዳዊት የተባሉ ኢንቨስተር፣ ኣሁን ኣቶ ዳዊት በህውሃት ባለስልጣናት 200 ሺ ብር በላይ ገንዘባቸው እንዳይንቀሳቀስ ተደርገዋል፣እኛም ይህንን ሃቅ የሚያጣራ የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን። ኣቶ ዳዊት ኣድዋ ከተማ ውስጥ የተሰጣቸው መሬት በክልሉ ሃላፊዎች ተነጥቀዋል፣እኛም ይህንን ሃቅ የሚያጣራ የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን።
~~ምርጫ በመጣ ቁጥር ለሚገደሉት የዓረና ኣባላት ማን እንደገደላቸው ለምን እንደተገደሉ ይህንን ሃቅ የሚያጣራ የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን።
~~ኢፈርት የትግራይ ህዝብ ነው ለሚሉ የህውሃት ባለስልጣናት የትግራይ ህዝብ መሆንዋን ኣሁን ድርቅ በተከሰተበት ወቅት ለምን ሁሉም ከትርፍ ድርሻ እንዳልተሰጠው የሚያጣራልን የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን!!!!!
~~ህውሓት ጉባኤ ባካሄደበት ወቅት ጌታቸው ኣሰፋ ላቀረበው መከራከሪያ ነጥብ “ክራይ ሰብሳቢነት ሙስና” ለምን በ ኣብዛኛው የህውሃት ማእከላይ ኮሚቴ እንዳይታይ እንደተደረገ የሚያጣራ የቪኦኤ ጋዜጠኛ እንፈልጋለን።
~~እናማ ግርማይ ገብሩ የፌደራሊዝም መብቱን ተጠቅሞ ከትግራይ ወሎ ድረስ ያስኬደው ትግራይ ውስጥ እንደዚህ ያለ ጥናት ቢያደርግ ላንዲትም ቀን እንደማይኖራት ስለሚያቅ ነው፣ ግርማይ ከመቀሌ ውጭ ወደ ተለያዩ የትግራይ ዞኖች ይሁን ወረዳዎች ለመንቀሳቀስ ከክልሉ ፍቃድ ያስፈልገዋል፣ ኣማራ ክልል ለመሄድ ግን መብት ኣለው፣ የአማራ ክልልም ትግራይ ውስጥ መብቱ ታፍኖ የውሸት የጋዜጠኝነት ስራውን በክልላቹ እንዲሰራ ስለፈቀዳቹለት እናመሰግናለን፣ ግ ርማይ ገብሩ ትግራይ ውስጥ ስንት የሚጣራ ነገር እያለ ውሎ ድረስ ምን ኣስኬደህ?  

No comments:

Post a Comment