Monday, November 9, 2015

በቦረና ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ

ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነገረ ኢትዮጵያ የዞኑን ሰብሳቢ ጠቅሶ እንደዘገበው በገላና ወረዳ የወረዳውን ሰብሳቢ አቶ በድሉ መንግስቱን ጨምሮ 10 የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታስረዋል።ጥቅምት 24/2008 ዓ.ም የታሰሩት የድርጅቱ አባላት ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውንና በቤተሰብም አለመጎብኘታቸውን ዘግቧል። የወረዳው ሰብሳቢ አቶ በድሉ መንግስቱ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚደርሳቸው ለፖሊስ ሲያመለክቱ ቢቆዩም ምንም ምላሽ ሳያገኙ ቀርተዋል።

No comments:

Post a Comment