Friday, November 27, 2015

የአዲስ አበባ የተለያዩ ወረዳዎች ተወካዮች የተባሉ መንግስት አይሰማንም አሉ

ኢሳት ዜና :-ሁለተኛውን የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አስመልከቶ የህዝብ ተወካዮች ናቸው ከተባሉ ሰዎች ጋር የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በውይይቱ ተወካዮች በየአካባቢው የሚታዩ ችግሮችን ተናግረዋል። የህዝብ ተወካዮቹ ” ብንናገርም የሚሰማን መንግስት” የለንም ብለዋል።

ምንም እንኳ ብዙዎቹ ተወካዮች ለገዢው ፓርቲ ካላቸው ቀረቤታ እና በድርጅት አባልነት ተመርጠው የመጡ ቢሆንም ፣ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ በነበረው ስብሰባ፣ አንዳንድ ተወካዮች ወረዳቸው የገጠመውን ችግር በድፍረት አቅርበዋል።
አንድ የወረዳ 14 ተወካይ ፍትህ የሚጥስ አገዛዝ መኖሩንና ፣ የህዝቡን አቤቱታ የሚሰማ መሪ መጣታቱን ገልጸው፣ ወጣቱ መንግስትን እየጠላ ቢመጣ አይፈረድበትም ብለዋል
የወረዳ 3 ተወካይ በበኩላቸው በወረዳቸው የሚታዬው የውሃ ችግር አሳሳቢ መሆኑን ገልጸው፣ “ህዝብ ሲቆጣ ውሃው ይለቀቃል፣ ህዝብ ዝም ሲል መልሶ ይጠፋል” በማለት ችግራቸውን አሰምተዋል።
የመሬትና ካርታ፣ ህገወጥ ግንባታ በሚል የሚፈርሱ ቤቶች ጉዳይ እና የጸጥታ ጉዳይ የህዝቡ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች መሆናቸውን ስብሰባውን የተከታተሉ ወገኖች ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment