Monday, November 16, 2015

ሱዳናዊያን በኢትዮጵያ ታጣቂዎች ጥቃት እየደረሰብን ነው አሉ

ኀዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አቅራቢያ የጸጥታው ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱንና በሱዳናዊያን በግፍ ለተገደሉት ኢትዮያዊያን አፋጣኝ አጸፋዊ ምላሽ የሰጡት የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ታጣቂዎች ሃምሳ መንደሮችን በቁጥጥራቸው ስር ማድረጋቸውንና ሃያ ለሚሆኑ ያገቷቸውን ሱዳናዊንን 360ሺህ የሱዳን ዲናር ማለትም 59 ሽህ ዶላር አስከፍለው መልቀቃቸው ተዘግቧል። የገዳሪፍ የግህ አውጭ ካውንስል ሊቀመንበር የሆኑት ሞሃመድ ኤል ማርዲ፣ ሰፊ መሬት የተቆጣጠሩት የኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች እንዲወጡ የጠየቁ ሲሆን፣ የሚሊሺያዎችን ማንነት ግን በውል አልገለጹም።

በገላባት፣ ኤልፋሻጋና ገዳሪፍ አካባቢ ያሉት ሱዳናዊያን ሁኔታውን በመፍራት መኖሪያ ቀያቸውን በመልቀቅ መሸሻቸውንና በአካባቢው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መሰማራቱንም ኦል አፍሪካ ዘግቧል። ባለስልጣኑ አስቸኳይ የድንበር ማካለል እንዲጀመር ወትውተዋል። ኢህአዴግ ሰፊ ግዛት ለሱዳን መንግስት ቢሰጥም፣ ኢትዮጵያውያን ግን አልተቀበሉትም።

No comments:

Post a Comment