Friday, November 20, 2015

በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች ዜጎች በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ነው

ኀዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአለማቀፍ ድርጅቶች ችግሩ አሳሳቢ መሆኑን እየገለጹ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ችግሩ አስከፊ ሆኖ ቀጥሎአል።

በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኙ አርብቶአደሮች በድርቅ፣ ከግልገል ጊቤ ግድብ ግንባታና በአካባቢው የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከመከላከያ ሰራዊት በሚደርሰው ጥቃት፣ ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን የደቡብ ኦሞ ህዝብ ድርጅት ምክትል ሰብሳቢ አቶ አለማየሁ መኮንን ተናግረዋል።በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ወሎ አካባቢ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ምግብ እየቀረበ መሆኑን የክልሉ ህዝብ ግንኙነት ሃአለፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ተናግረዋል ።
ክልሉ በዚህ አመት ከፍተኛ የግብርና ምርት እንዳገኘ ቢገልጽም፣ አቶ ብናልፍ ግን ከፍተኛ የምርት መቀነስ ማጋጠሙን ገልጸዋል። በክልሉ የምግብ እርዳታ እየቀረበ አይደለም በማለት በሌሎች ባለስልጣናት ሲሰጥ የነበረውን መግለጫም አስተባብለዋል።
በሌላ በኩል 13 ወጣት ጋዜጠኞችና ጻሃፊዎች ህዝባቸውን ለመታደግ የሚያስችል ኮሚቴ ማቋቋማቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። ጋዜጠኞቹ ቤዛ እንሁን የሚል ድርጅት መስርተው እርዳታ ለማሰባሰብ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ለኢሳት ገልጿል። ድርቁን በተመለከተ ያደረግነውን ቃለምልልስ ከዜናው በሁዋላ እናቀርባለን።

No comments:

Post a Comment