Friday, November 27, 2015

ከአንድ ሺ ያላነሱ የአዲስ አበባ ፖሊሶች የሥራ መልቀቂያ አስገብተው በመጠባባቅ ላይ ናቸው

የፖሊስ ምንጮች እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ስራቸውን ለመልቀቅ ማመልከቻ ያስገቡ ፖሊሶች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል።7 አመት ያላገለገሉ ፖሊሶች ያገለገሉበት ዘመን ታስቦ ገንዘብ ከፍለው የሚሰናበቱ ሲሆን፣ ይህንን ክፈተት በመጠቀም ብዙዎች ስራውን እየለቀቁ ሄደዋል። ከፖሊስ የሰው ሃይል ክፍል የደረሰን አስተማማኝ መረጃ እንደሚያሳያው መልቀቂያ አስገብተው ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ፖሊሶች 1 ሺ ይደርሳሉ። ብዙዎች ለመልቀቃቸው የሚሰጡት ምክንያት ከስራ ጫና፣ ከአስተዳደር፣ ዘረኝነትና ከደሞዝ ጋር የተያያዘ ነው።

ለቃቂ ፖሊሶች ተቃዋሚዎችን ሊቀላቀሉ ይችላሉ የሚል ስጋት የገባው መንግስት ሰሞኑን ለአመታት ላገለገሉ ፖሊሶች የአግልግሎት ሰርተፊኬት በመስጠት ፍልሰቱን ለማስቆም እየተሯሯጠ ነው።
ሰሞኑን በተሰጠው የአግልገሎት የምስክር ወረቀት አንዳንድ ፖሊሶች ከ1 እስከ አራት ወራት ያሉ ደሞዛቸውን በስጦታ መልክ ተቀብለዋል። ይሁን እንጅ ሽልማቱ የመልቀቂያ ጥያቄ የሚያቀርቡ ፖሊሶችን ቁጥር ሊቀንሰው አልቻለም።
አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ፖሊስ ፣እሱ በሚሰራበት ወረዳ በርካታ ፖሊሶች በመልቀቃቸው የስራ ጫና መፈጠሩንና በአለቆች ላይ ግምገማ መጀመሩን ተናግሯል። አማራጭ ቢያገኝ ስራው ላይ የሚቆይ ሰው አይገኝም ሲልም በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ገልጿል።

No comments:

Post a Comment