Thursday, January 8, 2015

“አሜሪካ በየቀኑ እየቀጠቀጠን በመሆኑ ብንችል ቪኦኤን ድምጥማጡን እናጠፋው ነበር” ሲሉ የብአዴን ዋና ጻሃፊ ተናገሩ

ታኀሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን ይህን የተናገሩት መጪውን ምርጫ አስመልክቶ ለተመረጡ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ለባለድርሻ አካላት ባደረጉት ገለጻ ነው።
አቶ አለምነው ነጻ ሚዲያ በሌለበት አገር ኢሳትና ቪኦኤን የመሳሰሉ ነጻ ሚዲያዎችን ማፈን ተገቢ ነወይ የሚል የጽሁፍ ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን፣ ቪኦኤ በአሜሪካ መንግስት ሳንባ የሚተነፍስ ነው ፣ የአሜሪካ መንግስት አላማ ደግሞ የሊበራሊዝም አላማ ነው በዚህም የነተሳ የኢትዮጵያን መንግስት ሌት ከቀን እየቀጠቀጠው ነው ብለዋል። የውጭ ባለሃብቶች መጥተው የኢትዮጵያን ባንክ መምጠጥ ይፈልጋሉ ያሉት አቶ አለምነው፣ ቴሌም በውጭ ቱጃሮች እንዲያዝ ይፈልጋሉ ሲሉ አብራርተዋል። ቴሌ ማለት ገንዘብ የሚያመርት ማሽን ነው የሚሉት አቶ አለምነው፣ ደርጅቱ በየአመቱ 6 ቢሊዮን ብር ለአባይ ግድብ ድጋፍ እንደሚያደርግና የአባይ ግድብም በቴሌ ትርፍ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። ታዲያ ይህን ነው አሜሪካኖች ሊቀሙን የሚፍለጉት ሲሉ ለተሰብሳቢው አስረድተዋል። እነዚህ ሚዲያዎች ቢችሉ ምድር እንዲገለባብጥ ፣ አገሪቱ የተኩስ አገር እንድትሆን ይፈልጋሉ ያሉት አቶ አለምነው ፣ አቅም ስለሌለ ነው እንጅ አቅም ቢፈቅድማ ድምጥማጣታቸውን ማጠፋት ነበር ብለዋል።



No comments:

Post a Comment