Monday, January 26, 2015

ወደ ኤርትራ በማቅናት ላለፉት ሶስት ሳምንታት በኤርትራ ድንበር የሚገኙ የኢትዮጰያ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ ሲቃኙ የቆዩት የኢሳት ጋዜጠኞች ትናንት እሁድ ተመለሱ።

ጥር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እና ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም የኢህዴግን መንግስት በትጥቅ ትግል ለመፋለም ብረት ያነሱ የኢትዮጰያ ተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ በዓይን ለማየት እንዲሁም ስለ ኢትዮጰያና ኤርትራ የወደፊት ግንኙነት የኤርትራ ባለስልጣናትን ቃለ ምልልስ ለማድረግ ወደ ኤርትራ ያቀኑት ከሶስት ሳምንታት በፊት መሆኑ ይታወቃል።
ፋሲልና መሳይ ባለፉት ሶስት ሳምንታት የኤርትራ ቆይታቸው የሄዱበትን ዓላማ በሚገባ ማሳካታቸውን ጋዜጠኛ ፋሲል ገልጿል። በኤርትራ ቆይታቸው ፌስ ቡክን ጨምሮ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሚሰጧቸው አስተያየቶች በሞራልም ሆነ በሀሳብ ሲያበረታቷቸውና ፍቅራቸውን ሲገልጹላቸው ለነበሩ ኢትዮጰያውያን በሙሉ ምስጋናቸውን ገልጿል።


No comments:

Post a Comment