Thursday, January 1, 2015

የደህንነት ሃይሎች ዜጎችን ለማደናገርና ለማስፈራራት የእጅ ስልኮችን መበርበር ሊጀምሩ ነው

ወያኔ ‘ሚስጥራዊ ‘ስብሰባዎች በተሰብሳቢዎች ሞባይል ስልኮች እየተቀረጹ በውጭ ባሉ መገናኛ ብዙሃን መቅረባቸውና የዘረኛው መንግስት ሚስጥርና የድርጅቱን ጉድፍ አጉልቶ በማሳየቱ ይህም ድርጊት የወያኔን አመራሮች እያበሳጨ በመምጣቱ በየቦታው በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ ተሰብሳቢዎች ምንም አይነት ሞባይል ስልክ ወደ አዳራሽ ይዘው እንዳይገቡ መከልከል ተጀምሯል። በሌላ በኩል ዛሬ ይፋ በተደረገው ዜና ላይ አራት ከፍተኛ ማእረግ ያላቸው የአየር ሃይል አብራሪዎች ከድሬዳዋ አየር ሃይል በመነሳት ኬንያ መግባታቸው እንደተሰማ የደህንነት ሃይሎችና የመንግስት ባለስልጣናት የበርካታ ሰዎችን የእጅ ስልኮችን ሲፈትሹ ውለዋል፣ ይህ የግለሰቦችን ስልክ መፈተሽ/ መበርበር ሰፋ ባለ ሁኔታ በየከተሞች ያሉትን ሰላማዊውን ሰው ለማሸበርና ለማሸማቀቅ ይረዳል ብለው በማሰብ የደህንነት ሃይሎች ከሰሞኑ በሰፊ ዘመቻ እንደሚጀምሩት የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል።


No comments:

Post a Comment