Saturday, January 24, 2015

አንዳርጋቸው ጽጌ ከሆንን እስከ ምን? ከAbraham Z,Taye

የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ የነበረው ጀግናው አቶ አንዳርጋቸው  ጽጌ በፋሺስት ወያኔ እጅ ከወደቀ  ወዲህ “እኔምአንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ” “ሁላችንም አንዳርጋቸው ነን” የሚሉ ተተኪ ሰዎች ተበራክተዋል። አንዳንዶች እንደፌስቡክ ባሉድረገጾች ሳይቀር ስማቸውን አንዳርጋቸው ጽጌ ብለው  ስሙንም ፎቶውንም በመጠቀም አንዳርጋቸው ነን ሲሉይታያሉ።አንዳርጋቸው ጽጌ ነን ስንል ስሙን ይዘን በማህበራዊ ድረገጾች በመጥራት ሲቀጥልም ፎቶውን በትልቅ ፍሬም አስርተንበየአደባባዩ ሰልፍ በመውጣት ባለፈ መሆን እንዳለበን ለማሳሰብ ከወጣትነቱና ከ አረጋዊነቱ ሁለት ጉልህ ክስተቶቹን በመምረጥ እንድንማርበት  ይሄ ጽሁፍ ተዘጋጅቷል።


በወጣትነቱ     የነጻነት ትግልን የጀመረው ገና በአፍላ ዕድሜው ነው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱን ከቀሰመበት ከተፈሪ መኮንን ት/ቤት የኢንጅነሪንግ ትምሀርቱን ከተከታተለበት የሃይለስላሴ/ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለ ንጉሱን ለመገለበጥከተወጠነው ታዋቂው የተማሪዎች ንቅናቄ አቀንቃኞች  አንዱ ነበር።የዘመኑ ወጣቶችስ አንዳርጋቸው ጽጌ ነን ካልን አምባገነኑን የወንበዴ ስርዓት ለመናድ ይህ ነው ተብሎ የሚጠቀስእንቅስቃሴ እያደረግን ነን ወይ? የሚል ጥያቄ በ አዕምሮዬ  ዘወትር  ይመጣል።በ 1960ዎቹ በነበረው አብዮት የባሌና የጎጃም ገበሬዎች ንጉሱ ላይ ካደረጉት አመጽ በተጨማሪ በመሃል ሃገርአብዮቱን ካቀጣጠሉት መስዋዕትም ከሆኑት ከተማሪዎቹ እንደ ጥላሁን እንደ አለልኝ ወዘተ ቆራጦች ላለመሆን ምንያዘን?ያኔ “መሬት ላራሹ” ይሁን ማለት አንገብጋቢ አጀንዳ ነበር። አሁንም የባሰበት ሁኔታ ነው ያለው። መሬታችን ለህንድለፓኪስታን ኢንቨስተሮች እየተሰጠ ከመኖሪያም እያፈናቀሉን ነው። ከከተማም ከገጠርም ዕትብታችን ከተቀበረበትሲያፈናቅሉን ተመጣጣኝ ካሳ አይሰጠንም።የዘውድ ስርዓታቸው ሲገረሰስባቸው  ያኔ የነበሩት  ነገስታቱም መኳንንቱም ኢትዮጵያዊ ስሜት የነበራቸው ቅንጣትምመሬት ለውጭ ያልሰጡ በቅኝ ያልተገዛች ኢትዮጵያን ዳርድንበሯን ያስከበሩ መሆናቸው የማይካድ ሃቅ ነው።ዘመነኞቹቅኝ ገዢዎቻችን ግን ዳር ድንበሯን ያስረከቡ ኢትዮጵያችንን እያፈርሱ ያሉ  ዘረኛ ፋሺስት ባንዳዎች ናቸው።ይህንን ጸረ ኢትዮጵያ ኣቋም ያለውን አገዛዝ  ወያኔን ብቻ ሳይሆን የደርግንም ስርኣት በመቃወም ኢ ህ አ ፓን የተቀላቀለጀግና አርበኛ ነበር አቶ አንዳርጋቸው በወጣትነቱ። በቀይሽብር ታናሽ ወንድሙን አምሃ ጽጌን ያጣው አንዳርጋቸውበስደት ምድረ አውሮፓ እንግሊዝ በውርዝውናው ተጠልሏል። እኛም አንዳርጋቸው ጸጌ ነን ስንል አሱን የሆንነው እንደአንዳርጋቸው ለስደት የተዳረግን በመሆናችን ብቻ እንዳልሆነ ማሳየት አለብን።ምክንያቱም እሱ  በዘመነ ደርግም በዘመነ ኢህአዴግም ስለ ኢትዮጵያ ነጻነት ስለ ሰባዊ መብት ስለ ሃገር አንድነትከማሰብ ፤ከመስራት የማይቦዝን ትልቅ ስብዕና ያለው ነው።በራሱ አንደበት ከተናገረው ውስጥ ወያኔዎች በጣም የሚፈሩት እሱ የነሱን ደካማ ጎን በጣም ያውቃል ብለውስለሚሰጉ ነው። የወያኔን ጠንካራና ደካማ ጎን አጥንተን ጨርሰናልን? ደርግ እንደተወገደ ሃገር አለኝ ብሎ ከጉያቸውገብቶ ለሁለት አመት ያልበለጠ በአዲስ አበባ መስተዳድር አባላቸው  ሰርቷል። ዳካማነታቸውን አይቶዘረኝነታቸውን ነቅፎ መውጣቱ ለሆዳም የወያኔ ካድሬዎችም የሚያስተላልፈው ትልቅ መልዕክት አለ። እስከመቼ የባንዳ ባንዳ ሆናችሁ ትኖራላችሁ ይላቸዋል መልዕክቱ።ከተራ የወያኔ ካድሬ እስከ መከላከያው ሰራዊት ወንድሞቹሲገደሉ ዝም ብሎ ከማየት ጥይት ከማቀበል አምባገነኑን ስርዓት ነቅፎ እንደ አንዳርጋቸው መውጣት እኔምአንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ ስንል የሚሰማንን  ቢያንስ የህሊና ነጻነትን ያጎናጽፋል።

በ አረጋዊነቱ      በ1997 ምርጫ ዋዜማ ባወጣው  “ነጻነትን የማያውቅ ነጻ ኣውጪ” መጽሃፍ ፥ የቅንጅት ለ አንድነትና ለዴሞክራሲፓርቲ ሲመሰረት የተጋበዘ ከዚያም ዝዋይ ታስሮ ከተፈታ በኋላ የቅንጅት ታሳሪዎች እንዲፈቱ የተባበሩት መንግስታትንየኣውሮፓ ህብረትን ሳይታክት የጎተጎተ ፤ ከዚያም የግንቦት 7  የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መስራችና ዋናጸሃፊ መሆኑን ስናይ ምሁራን ተሰኝተው ለሃገራቸው በይፋ ከመስራት የሰነፉ አዛውንቶች በምንም መስፈርትየማይደርሱበት ዕንቁ ሰው ነው። እነዚህ ሰዎች እንኳን አንዳርጋቸው ጽጌ ነን ሊሉ ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት ይቅርናስለነጻነት ሰለዲሞክራሲ ቢያንስ በብዕር ስም  ለመጻፍ ካልሞከሩ የታሪክ ተወቃሾች ናቸው። አንዳርጋቸው ሸምግሎእንኳ ጉልበቱን እያሳየ ነው።እኛም ብንሆን አንዳርጋቸው ጽጌ ነን ከማለታችን ባለፈ የታሰሩት ይፈቱ የመሬት ቅርምቱ ይቁም ሰብዓዊ መብት ይከበርብለን በሰላማዊ ሰልፍ መላ አለምን ከማጨናነቃችን በዘለለ ኢትዮጵያ ሆነ ኤርትራ መሬት ላይ ወርደን ብረትእስከማንሳትና ወያኔን  በአካል እስከመጋፈጥ ድረስ ልንታመን ይገባል።


በንጽጽር ለማጠቃለል ያህል  አቶ አንዳርጋቸው ከሞቀው የኣውሮፓው ኑሮ ቤተሰቡን ልጆቹን ትቶ በረሃ ለበረሃ ሲንከራተት በየመኖች ለወያኔ ተላልፎ የተሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጆች ለማዳን ከሰማይ ወደምድር ወርዶ በይሁዳ ለሰቃዮቹ ተላልፎ በመሰጠቱ ለሰው ልጆች ሁሉ ያጎናጸፈውን ነገረ ድህነት ያንጸባርቃል። አንድርጋቸው ጽጌ ነን ስንል ተደላድሎ በምዕራቡ አለም መኖር ሳይሆን ዝቅ ብሎ ለኢትዮጵያ ሲሉ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘት ነው። እንደሱ ከንግስናቸን ዝቅ ብለን  በጫካ ፋቲክ የምንለብሰው፥እንጨት የምንፈልጠው፥ዉሃ የምንቀዳው አንዳርጋቸውን ነጻ ለማውጣት ሳይሆን ራሳችንን ነጻ ለማውጣትና በሃገራቸንም ሆነ በሌላው ሃገር እንደፈለገን ሳንታፈን  የመውጣት የመግባት መብት እንድናገኝ መሆኑ የሚሰመርበት ጉዳይ ነው።አንድርጋቸው ጽጌ ነን ስንል እሱ ከሰላሳ አመት በላይ እንደተሰደደው እኛም ሰደትህን ቀምሰናል ወይም እሱ ነጻነት የማያውቅ ነጻ አውጪን መጽሃፍ እንደጻፈ ሁሉ እኛም የድረ ገጽ አርበኛ ሆነናል በማለት ብቻ ሳይሆን እሱ አሳዳጆቹን ምሳቸውን ለማቅመስ ወደመሬት እንደሄደ ሁሉ እኛም በመሬታችን ኢትዮጵያ የሚጨበጥ ስራ መስራት ይጠበቅብናል።አቶ አንዳርጋቸው ከውርዝውና እስከ አረጋዊነቱ መላ ህይወቱን ስለ ኢትዮጵያ የሚያስብ፥ ሰለኢትዮጵያ የሚናገር ሰለ ኢትዮጵያ የሰራ እንደመሆኑ መጠን አንዳርጋቸው ነን ስንል  ውያኔን አስወግደን ለሃገራችን ነጻነት ዲሞክራሲ ፍት ህ እስኪሰፍን ድረስ መሆን አለበት።

No comments:

Post a Comment