Friday, January 23, 2015

መጪው ምርጫ በአድማ ብተና ስም እየተሰጠ ያለውን ስልጠና የተቃወሙ 97 የፌዴራል ፖሊስ አባላት እርምጃ ሲወሰድባቸው፤ 119 ፖሊሶች በግዳጅ እረፍት እንዲወጡ ተደረገ። ደረጀ ነጋሽ

ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር የተባረሩት አብዮታዊ ዲሞክራሲን መቀበል ያልቻሉ ናቸው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ፖሊሶችና ሚሊሻዎች ከምርጫው ጋር በተያያዘ ሊነሱ ይችላሉ የተባሉ ህዝባዊ አመጾችን ለማክሸፍ ያስችላል የተባለ የተኩስ ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ ከየክልሎቹ የመጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት በፌድራል ፖሊስ አድማ ብተና አደረጃጀት በየክልሉ የሚካሄደውን ይህን ስልጠና፦ << የፖሊስን ተልእኮና ዓላማ የሳተ ነው>> በማለት በርካታ የፌዴራል ፖሊስ አባላት እንደተቃወሙት በፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ያሉ የኢሳት ምንጮች ጠቁመዋል። ተቃውሞ ካነሱት መካከል 206 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተገምግምው ከስልጠናው እንዲወገዱ መደረጋቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል። ከነዚህ መካከል በ97ቱ ላይ እርምጃ ሲወሰድ፤119ኙ እስከ ምርጫው መጠናቀቅ ድረስ የግዳጅ እረፍት እንዲወጡ ተደርጓል።
የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄነራል አቶ አሰፋ በዩ እርምጃ የተወሰደባቸውንና የግዳጅ እረፍት እንዲወጡ የተደረጉትን የፌዴራል ፖሊስ አባላት አስመልክተው ለኢህአዴግ የምርጫ ጊዚያዊ ኮሚቴ በላኩት ደብዳቤ ፦<<አብዮታዊ ዲሞክራሲን መቀበል ያልቻሉ ናቸው>> ማለታቸውም ተመልክቷል። በመሆኑም በምርጫው ዸህንነት ጥበቃ ላይ እንዳይሳተፉ መታገዳቸውን ዳይሬክተሩ በደብዳቤያቸው ገልጸዋል።
ምንጮቻችን እንደሚሉት ግን <<አብዮታዊ ዲሞክራሲን መቀበል ያልቻሉ>> በሚል ምክንያት ከስራቸው እንዲታገዱም ሆነ በግዳጅ እረፍት እንዲወጡ የተደረጉት በብሄራቸው እየተመረጡ <<ለስርዓቱ ታማኝ አይደሉም፣ ግርግር ከተነሳ ሊከዱን ይችላሉ>>ተብለው የተጠረጠሩ ፖሊሶች ናቸው። ይህ በእንዲ እንዳለ በአማራ ክልል በከፍተኛ የስራ እርከን ላይ የሚገኙ የስራ ሂደት ሃላፊዎችና ካድሬዎች ትናንት ሀሙስ እና እና ዛሬ በምርጫው ዙሪያ ስብሰባ ማድረጋቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል።


No comments:

Post a Comment