Thursday, January 22, 2015

የኢህአዴግ ሴራ ከሸፈ::የኢህአዴግና የምርጫ ቦርድ ድራማ ተዋናይ እያጣ ነው::እናት ፓርቲያቸውን ይቅርታ በመጠየቅ ተመልሰዋል፡፡

የኢህአዴግ ሴራ ከሸፈ::
አቶ አየለ ስሜና አቶ ኢሳይያስ ቱሉ እናት ፓርቲያቸውን ይቅርታ በመጠየቅ ተመልሰዋል፡፡

የኢህአዴግና የምርጫ ቦርድ ድራማ ተዋናይ እያጣ ነው::ምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ጻፍኩለት ያለውን አየለ ስሜን አጥቷል :: ምርጫ ቦርድ ለአቶ አየለ ስሜ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ደብዳቤ መስጠቱን የምርጫ ቦርድ ምክትል ሀላፊ አቶ አዲሱ ገ/እግዚአብሄር ከዚህ ቀደም መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ዛሬ በምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ተሰጥቷቸው የነበሩት አቶ አየለ ስሜና አቶ ኢሳይያስ ቱሉ እናት ፓርቲያቸውን ይቅርታ በመጠየቅ ተመልሰዋል፡፡ከእነ አቶ አየለ ቀደም ብለው የተወሰኑ ወጣቶች ከፓርቲው ውጪ ይሰበስቧቸው የነበሩ ሰዎችን የጥፋት ተልዕኮ በመረዳት መመለሳቸው አይዘነጋም፡፡
በእኔ እምነት ከዚህ ቀደም በፓርቲው ውስጥ በተደረገ ምርጫ ለራሳቸው የሰጡትን ድምጽ ብቻ ያገኙት አቶ ትዕግስቱ አወሉ ብቻቸውን ከመቅረታቸው በፊት እነ አየለ ስሜን በመከተል ይቅርታ እንደሚጠይቁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

No comments:

Post a Comment