Thursday, January 29, 2015

ከመንግስታዊ አሸባሪው ወያኔ መልካም ነገር መጠበቅ ከእባብ እንቁላል ነጭ እርግብ የመጠበቅ ያህል ነው::

ወያኔ እንደ ኢዴፓ አይነቶችን ተለጣፊ ፓርቲዎች መቀፍቀፉን ተያይዞታል::በሰላማዊ ትግል ላይ የተሰማሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ እየደረሰ ያለው መንገላታት እና ወከባ በአሁኑ ወቅት ፓርቲዎቹን እስከማፍረስ እና አባላትን እስከመበተን ጉዞ ተይዟል::ይህ በፓርቲዎች ላይ የሚፈጸመውን መንግስታዊ ሽብርተኝነት እጅግ በከፋ መልኩ ቀጥሎ ይገኛል::

አንድነት ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የደረሰዉን ጉዳት በተመለከተ መግለጫ እየተሰጠ ሲሆን የተጎዱ አመራሮች እና አባላት ዝርዝር መግለጫ እየሰጡ ነው::መድረኩን የተከበሩ አቶ ተመስገን ስምረትይ አቶ ብሩ እና አቶ አስራት አብርሃም ሲመሩት ዝርዝር መግለጫ እየተሰጠ ነው:: የወያኔው ኢቢሲ ጣቢያ ለመግለጫው ሳይጠራ በቦታው ደርሶ እንዳይገባ የተደረገ ስለሆነ በደጅ ቀረጻ እያደረገ ነው::



ከወያኔ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የጠበቃችሁ፤ ከወያኔ ሥልጣን መጋራት የፈለጋችሁ፤ ከወያኔ የእምነት፣ የፕሬስና የሃሳብ ነጻነት የጓጓችሁ፤ ‘ከወያኔ ጋር ተስማምቶ መሥራት ይቻላል’ የምትሉ፤ እንኳን አብሮ ለመሥራት ለመወዳደር እድል የማይሰጥ ፈሪ ድርጅት መሆኑን በይፋ አረጋግጧል። ከወያኔ ጋር አንድ ነገር ብቻ ነው የሚቻለው፤ ከወያኔ በታች ሆኖ መሥራት። ጫማ እየላሱ ‘ጌታዬ!’ ማለት። ያንን የሚመርጥ የፖለቲካ ድርጅት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደፈለገ መንቀሳቀስና መሥራት ይችላል። ጥሩ ቢሮ ይሰጠዋል። ግዙፍ ባጀት ይመደብለታል። ዓመታዊ ጉባዔውን ሼራተን መደገስ ይችላል። በየምክንያቱ ቤተመንግሥት መግባት መብቱ ይሆናል። የመገናኛ ብዙሃን ችግር አይገጥመውም። እስር፣ ዛቻና ወከባ ሕልም ሆነው ይቀሩለታል። ‘ባሪያ የተቃዋሚ ድርጅት’ እየተባለም ይወደሳል።

ወያኔ ሃብትና ሥልጣን አያጋራም። ሁሌም የበላይ ሆኖ ሌሎችን መምራትና መቆጣጠር ብቻ ነው የሚፈልገው። ሌሎቹ እሱን እንዲያጅቡት ነው እቅዱ። ለሚቀጥሉት ብዙ ዓመታትም ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ለመታየት የሚያስችለውን እርምጃ ሁሉ ከመውሰድ አይመለስም። ወያኔ ገንዘብ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ዘራፊዎች የሚሰበስበው፣ ከትላልቅ ሃገራት የጸጥታ ድርጅቶች ጋር የሚሰራው፣ ከአለም አቀፍ አሸብር እና ወንጀለኛ ድርጅቶች ጋር በጋራ የሚንቀሳቀሰው ፣ ሰላማዊ ዜጎችን እያፈሰ በአሸባርነት የሚወነጅለው ፣ ገንዘብ እየረጨ በየመንደሩ የራሱን ሚሊዮነር የሚቀፈቅፈውና ሰራዊቱን የሚያንጸው ለሃገር ብሎ አይደለም። ለአንድ ግልጽ ዓላማ ነው፤ ሥልጣኑን ላለማጋራት፤ ሥልጣን አጠገብ ማንንም ላለማድረስ! …..ያ መታመን ያለበት እውነት ነው።

በምንም ተአምር አትታለሉ፤ ወያኔ በምንም ሁኔታ ሥልጣኑን አሳልፎ ለማንም አይሰጥም። ከተለያዩ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የፈለገ ዓይነት ስምምንነት ቢያደርግ፣ ሥልጣኑን ያጋራል ማለት አይደለም። ቁራሽ ሥልጣን ጠብቃችሁ ከሆነ ዳግም ተሞኝታችኋል። በዚህ አጋጣሚ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር በሽብር የታወቀው ሕወሓት ከወደቀ የብአዴን እና ኦሕዴድ በህይወት መኖር ያበቃለታል።ስለዚህ እያንዳንዳችን ኢሕአደግን ወደ ከርሰ መቃብር ለመክተት በሙሉ ሃይል ተባብሮ በመታገል የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነት ማረጋገጥ የእያንዳንዳችን ሃላፊነት እና ድርሻ መሆኑን መገንዘብ ግደታችን ነው። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!! ‪

#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment