Monday, January 5, 2015

አንድ የአየር ሃይል አብራሪ ተቃዋሚዎችን መቀላቀሉ ተሰማ 

አንድ የአየር ሃይል አብራሪ ተቃዋሚዎችን መቀላቀሉ ተሰማ ባለፈው ረቡዕ ታህሳስ 15፣ 2007 ዓም ኢሳት 4 የአየር ሃይል አብራሪዎች ወደ ኬንያ ማምራታቸውን በሰበር ዜና ካቀረበ በሁዋላ፣ አንድ ተጨማሪ የአየር ሃይል ባልደረባ ጠፍቶ ተቃዋሚዎችን መቀላለቀሉ ተሰምቷል። ባለፈው ሮብ የጠፉት የሚግ 23 አብራሪ ሻምበል ገዛሃኝ ደረሰ፣ የኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አብራሪ ሻምበል ዳንኤል ግርማ፣ የኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አብራሪ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጠ፣ የኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር ብሩክ አጥናኤ በአጥሩ የደህንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።

No comments:

Post a Comment