Wednesday, January 28, 2015

ሄሊኮፕተር በመያዝ ወደ ሶስተኛ አገር የጠፉት የአየር ሃይል ባልደረቦች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገለጹ

ጥር ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ወር ሄሊኮፕተር ይዘው የጠፉት ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ እና ቴክኒሻን ጸጋ ብርሃን ግደይ በተረጋጋ እና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለኢሳት ገልጸዋል።
ፓይለቶቹ በሚገኙበት ሶስተኛ አገር ውስጥ ሆነው ከኢሳት ጋር ግንኙነት የመሰረቱ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረገው የነጻነት ትግል አስተዋጽኦ ለማድረግ መዘጋጃታቸውን ተናግረዋል።
ሶስታችንም በአንድ ላይ የምንመደብበትን ጊዜ ስንጠብቅ ቆይተን ነበር ያሉት ፓይለቶቹ፣ አጋጣሚው ሲፈጠርላቸው ቀደም ብሎ ባወጡት እቅድ መሰረት መጥፋታቸውን ገልጸዋል።
ጉዞአቸውን ወደ ሶስተኛ አገር በሚያደርጉበት ወቅት ከራዳር እይታ ውጭ ለመሆን እስከ 10 ሜትር ድረስ ዝቅ ብለው መብረራቸውን የገለጹት ፓይለቶቹ፣ ካሰቡበት ቦታ ሲደርሱ ነዳጃቸው ማለቁን ተናግረዋል።
ለምን ወጣችሁ ተብለው የተጠየቁት ፓይለቶቹ፣ በአየር ሃይል ውስጥ የሚታየው ዘረኝነት፣ አድልዎና የአስተዳደር መበላሸት ይህን ውሳኔ እንዲወስኑ እንዳስገደዳቸው ገልጸዋል።
እድሉ ቢገኝ አብዛኛው የአየር ሃይል አባል ስርአቱን ትተው ለመውጣት ዝግጁ መሆናቸውን ፓይለቶቹ ገልጸዋል። ፓይለቶቹ ሁኔታዎችን አመቻችተው ለኢሳት ቃለምልልስ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
በሌላ ዜና ደግሞ የኢሳት የጋዜጠኞች ኤርትራ በተገኙበት ወቅት በተለያዩ ወራት ኤርትራ የተገኙነትን በርካታ የአየር ሃይል አባላት አነጋግረዋል።
የሱ 27 እና የሚግ 23 አብራሪዎችን ጨምሮ በርካታ የተዋጊ ሄሊኮፕተር ፓይለቶች ኤርትራ ከሚገኙ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር በመቀላለቀል በመታገል ላይ ናቸው። ኢሳት ከፓይለቶች ጋር ያደረገውን ቀለምልልስ በቅርቡ ይለቃል።


No comments:

Post a Comment