Tuesday, January 13, 2015

ዶር ዳኛቸው አሰፋ ከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ አለች ወይ?

አንድ የተማረ ሰው ከ አዲስ አበባ ወጥቶ ወደ ሌላ ክልል ሄዶ ስራ ሲሰራ ደሞዙ ተቆርጦበት ወይም ዘግይቶበት ሰለ መብቱ ቢጠይቅ የሚሰጠው ምላሽ እኔዴውም ከ አላገራቹህ መጥታቹህ ስራ ስላገኛቹህ ልታመሰግኑ ይገባል ይባላሉ፥፥ አሁን ያለንበት ደረጃ አሥከፊና አስቸጋሪ ነው፥፥ እነዴውም አሁን እየጠየቅን ያለነው፥ አገራችን አለች ወይ ነው? ኢትዮጵያ አለች ወይ? ልክ ከ አዲስ አበባ ወጣ ስትል ከየት ነው የመታኽዉ ትባላለህ፥፥ ልክ ሌላ አገር የሄድክ እስኪመስልህ፥፥ ምንም አይነት ፕሮቴከሽን የሌለባት አገር ሁናለች፥፥ መጀመሪያ የጠነሰሱት ቢህል አሁን እያበበ ነው፥፥ የ አገሪቱ ሁኔታ ኢዝ አት ስቴክ (is at stake)፥፥ አንተ ትቀልዳለህ ሶማሊያ :ጋምቤላ ተወው፥ እዚህ አምቦ እንኮ የኔ ተማሪወች ስራ ተቀጥረው የ እኛ ተማሪወች እስኪመጡ ብቻ ነው ስራ ሊኖራቹህ የምትችሉ ነው የተባሉት፥፥ አንተ ትቀልዳለህ! አገር የለንም ነው እንኮ የምልህ፥፥ ይህ ከ ሗላ ኪሴ አውጥቼ የምንገርህ እንድይመስልህ ልጄ፥፥
62(ስልሳ ሁለት) አመቴ ነው፥፥ ያለው እወነታ ይህ ነው፥፥ አገር የሚባል ነገር አብቅቷል፥፥ ኣዝናልሁ ግን ያለው ሁኔታ ይህ ነው፥፥ህገ መንግስቱ ዜጋ የሚባል ቮካቡላሪ የለውም፥፥ እኛ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ነው የሚለው፥፥ አንድ ሰው በግልሰብ በዜግነት ስለ መብት የሚያወራበት ሁኔታ የለም፥፥በጣም በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው፥፥ ወጣ ካልክማ፥ አንተ እንዴት መጣህ? ይልሃል፥ ቱሪስትን ነህ ወይስ ምንድን ነህ? ይልሃል፥፥ ከየት ነው የመጣህ ነው እንኮ የምትባለው፥፥ የሚገርም ጉድ እንኮ ነው የፈላብን፥፥

አካዳሚክ ፊርደም የሚለውን ኮምፒሊትሊ አውጣው፥፥ ሁሉም ፕሮፌሰር፥ ሁሉም አስተማሪ አንገቱን ደፍቶ ዛሬ ነገ ያዙኝ ብሎ የሚኖርበት አገር ነው ዩኒቨርሲት ማለት ኢትዮጵያ፥፥ እነግራሃለው፥ የፈልጉትን ይበሉ እነግረሃለው፥ ይሄ ነው ያለው፥፥ስለ ሰቆጣ የጻፈው የህግ አስተማሪ ደብዳቤ ነው የተጻፈለት እንዲባረር፥፥ ያውም እሱ የብአዴን አባል ነው ምናምን ነገር፥፥ አካዳሚክ ፍሪደም የሚባል ቮካቡለሪወም የለ፥፥ ድሮ ቀረ፥፥ አሁን ሳምንት ምን አለኝ ቸርማኑ እና እኛ እንመርጥና እነሱ ሪኮሜንድ ያደርጉልናል፥፥ቼርማን አንመርጥም፥ ዲን አንመርጥም፥ ካድሬወች ነው የሚመርጡልን፥ ምን አለፋህ፥፥አንድ ዩኒቨርሲቲ አድሚሽኑን (admission) ያስረከበ ዩኒቨርሲቲ አካደሚክ ፍሪደም አለኝ ይላል እንዴ? በትዛዝ እንከሌን ተቀበሉ እነከሌን አተቀበሉ የሚባል ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፊሪደሙን ተወው አልኩህ፥፥እርሳው እሱን ፥ ይገባሃል የምልህ? አድሚሽኑን ያስረከበ ዩኒቨርሲቲ አካደሚክ ፍሪደም አለ ብሎ ሊያወራ አይችልም፥፥

መከፋፈልን እንደ ጸጋ የወሰደ ስርዓት እኮ ነው፥፥ምን ትጠብቃለህ እስኪ ንገረኝ፥፥ “የኢትዮጵያ ህዝቦች እንኳን ደስ ያላቹህ ብሄር ብሀረሰቦች ሆናቹህ ነው እኮ የሚለው፥ ዘፈኑ ሁሉ”፥፥አንተ ነገሩን እንዴት ነው የምታየው፥፥ አገር የለም፥ ህግ የለም፥ እየጠፋን ነው ምን ትላልለህ፥ ስለመብት ታወራለህ እንዴ፥፥ የእኛስ የተማሪወች ማህበር አለ አይደል እንዴ ካድሬወች ነው እንኮ ራን የሚያደርጉት፥፥ ሲቪል ማህበራት የሚባል ነገር የለም፥፥ ወይ ጠፈተዋል ወይ ተካተዋል


No comments:

Post a Comment