Friday, January 16, 2015

የወልቃይት ህዝብ ለመንግስት ጥያቄ አቀረበ።

የወልቃይት ህዝብ ለመንግስት ጥያቄ አቀረበ።
(ኢሳት ዜና)፦የወልቃይት ህዝብ እየደረሰበት ላለው የፍትህ መጓደል፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የከፋ በደል እና መገፋት ተገቢው ምላሸ በቶሎ እንዲሰጠው ጥያቄ መቅረቡን አስተባባሪዎቹ ገለጹ።
የአስተባባሪዎቹ ተወካይ ለኢሳት እንደገለጹት፣ የወልቃይት ህዝብ ከማንነቱ ጀምሮ በመልካም አስተዳደር እጦትና በፍትህ መጓደል የተጋረጡበት ፈተናዎች ምላሽ እንዲያገኙ፤ፌዴሬሽን ምክር ቤትንና የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤትን ጨምሮ ይመለከታቸዋል ለተባሉ በርካታ ድርጅቶችና መስሪያ ቤቶች፤ ባለፈው ታህሳስ ወር በደብዳቤ ጥያቄ ቀርቧል።
ባለ 18 ገጽ ደብዳቤ ከቀረበላቸው ድርጅቶች መካከል፦ ህወሀትና ብአዴን እንደሚገኙበት የጠቀሱት ተወካዩ፤እስካሁን ድረስ ከአንዳቸውም ምላሽ አለመገኘቱን ተናግረዋል።
(ድምጽከ5፤13 እስከ5፡37)
<<ስር የሰደደው ችግራችንና ገደብ ያለፈው በደላችን፤ በጥይትና በጠመንጃ ሳይሆን በሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንገድ እንዲፈታና ምላሽ እንዲያገኝ እንፈልጋለን፤ የማንም ህይወት እንዲጠፋ አንፈልግም>>ያሉት አስተባባሪው፤ << ሆኖም መንግስት ምላሽ ካልሰጠን፣ ህዝቡ የራሱን ምላሽ ይሰጣል>>ብለዋል።
(ከወልቃይት ህዝብ አስተባባሪ ጋር የተደረገው ቃለ-ምልልስ በልዩ ፕሮግራም የሚቀርብ መሆኑን እናሳውቃለን)


No comments:

Post a Comment