Tuesday, January 6, 2015

የወልቃይትን መሬት በተመለከተ በብአዴን አመራሮች መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል

ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ህዝብ መሬት በግፍ እየተቀማ ለትግራይ ነዋሪዎች ከትግራይ ህዝብም ለህወሀት ደጋፊዎች መከፋፈሉ ይታወሳል ይህንን ተከትሎ ላለፉት በርካታ አመታት የራያ፣ የሁመራ እና የወልቃይት ህዝብ ለስደት እና ለጥፋት የተዳረገ ሲሆን ከሰሞኑም የትግራይ ክልልን ለማስፋፋት በተደረገው ጥረት ተቃውሞ ያሰሙ የክልሉ ነዋሪዎች ለድብደባ እና ለእስር መዳረጋቸውን ተከትሎ የአካባቢውን ህዝብ ለማነጋገር ወደስፍራው አቅንተው የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ድርሶባቸው ወደባህርዳር መመለሳቸውን ተከትሎ በዛሬው እለት ከፍተኛ የብአዴን አመራሮች እና የክልሉ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ከቀኑ 4 ሰዓት ጀምሮ ባህር ዳር የክልሉ መስተዳደር የስብሰባ አዳራሽ ተገኝተው የነበረ ቢሆንም ስብሰባው ባለመስማማት እስከ 6፡30 ከተካሄደ በኋላ ተሰብሳቢው የተባለው መሬት የአማራ መሬት ነው የሚል አዝማሚያ በማሳየቱ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ የገቡት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከምሳ በኋላ ስብሰባው ሲጀመር ከፌዴራል መንግስት መመሪያ መምጣቱን ተናግረው የሚቀጥለው ቅዳሜ ጥር 2 በአቶ አዲሱ ለገሰ እና በአቶ በረከት ስምኦን ሰብሳቢነት ስብሰባው ከእንደገና እንደሚካሄድ ተናግረው ስብሰባውን በትነውታል።

ይህንን ዜና ከባህር ዳር ያደረሰኝ ግለሰብ እንዳረጋገጠልኝ ከሆነ የወልቃይት መሬት ጉዳይ የክልሉን ካድሬ ቁጭት ውስጥ እንደከተተው የታወቀ ሲሆን ቅዳሜ የሚፈጠረውን ጉዳይ ለመገመት አስቸጋሪ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል።


No comments:

Post a Comment