Saturday, January 10, 2015

የወያኔው ጁንታ አንድነት ፓርቲ በምርጫው እንዳይሳተፍ የፖለቲካ ውሳኔ አስተላለፈ::

አንድነት ፓርቲ በድጋሚ የምርጫ ቦርድን ደባ ለማክሸፍ ጠቅላላ ጉባዬ ጠርቷል::
– አንድነት ፓርቲን ከሰላማዊ ትግሉ ለማስወጣት የተደረገውን ደባ ተጋልጧል::

የወያኔው አምባገነን ጁንታ የአንድነት ፓርቲ በ2007 በሚደረገው ምርጫ ላይ እንዳይሳተፍ በሕወሓት/ኢሕአዴግ ፖለቲካዊ ውሳነ ተደርጎበት ወደ ምርጫ ቦርድ እንደተላለፈ እና ፓርቲውን ከምርጫው ለማስወጣት ደባ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተጠቆመ:: እንደ ምንጮቹ ከሆነ ሕወሓት/ኢሕአዴግ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን ከማሰር እና ከማንገላታት ጀምሮ እስከ ምርጫ ቦርድ ማሸማቀቀ እና ሰበብ ማብዛት ቢሞክርም አንድነት ፓርቲ ይህንን ሁሉ ተቋቁሞ በአሸናፊነት መገስገሱ ለገዢው ፓርቲ መደናገጥ በመፍጠሩ ፓርቲው በምርጫ እንዳይሳተፍ ውሳኔ ማስተላለፉን ተገልጿል::

የአንድነት ፓርቲ አደገኛ የሆነበት ሕወሓት/እሕአዴግ ምርጫ ቦርድን ተገን በማድረግ ከምርጫ ለማስወጣት እንዲሁም ተለጣፊ አንድነት ፓርቲ ለመመስረት በመጣር ላይ ሲሆን ዓላማው በአባላት፣ በደጋፊና በህዝቡ ውስጥ ውዥንብር ለመፍጠር ታሰቦ የሚካሄድ ፖለቲካዊ ደባ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ ባስተላለፈው መግለጫ እንዳለው በሀገራችን አስተማማኝ ሠላም እና ዘላቂነት ያለው ደህንነት የሚያረጋግጠው እንደ ምርጫ ቦርድ ያሉ ተቋሞች ነፃ፣ ገለልተኛ እና በህዝብ ዘንድ አመኔታ ሲጣልባቸው ነው፡፡ ይህ ተቋም አሁን በያዘው ሁኔታ ከቀጠለ ከታሪክ ተጠያቂነት አይድንም፡፡ ገዢው ፓርቲም ጧት ማታ የሚያባንነው ሕዝባዊ እምቢተኝነት መምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡

በመሆኑም አሁን ፓርቲያችንን ለመታደግ እና የቦርዱን የመጨረሻ ካርድ ለማስጣል አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተናል፡፡ ይህ ማለት የትግሉ መጨረሻ አይደለም፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያደረሰብንን የሕግ ጥሰት ይዘን በፍርድ ቤት ክስ እንመሰርታለን፡፡ እስከ አሁን ያለውን ሂደት ስናየው የቦርዱ ፖለቲካዊ ደባ ቀጣይ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ስለሆነም መላው አባሎቻችን፣ ደጋፊዎቻችን እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ለምንወስዳቸው ተከታታይ ፖለቲካው ውሳኔዎች እና እርምጃዎች ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን በአክብሮት እናስተላልፋለን፡፡ ብሏል አንድነት ፓርቲ::

እንደ ፓርቲው ምንጮች ምርጫ ቦርድ እና ኢህአዲግ ባሰማራው ጥቂት ቡድን አማካኝነት አንድነት ፓርቲን ከሰላማዊ ትግሉ ለማስወጣት የተደረገውን ደባ አቶ ብርሃኑ ይግለጡ እና አቶ መሳይ ትኩ ያጋለጡ ሲሆን ቭዲዮው ይለቀቃል ተብሎ ይጠበqaል::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

No comments:

Post a Comment