Monday, January 26, 2015

ወያኔ ፀገዴ ላይ ያካሄደው ስብሰባ ከሸፈ

የትግራይ ነፃነት ግንባር /ህወኃት/ ገና ከፅንስሱ ሲነሳ ለሙን የሰሜን ወሎን፣ ምዕራባዊ ጎንደርን እና ምዕራባዊ ጎጃምን በማካተት ታላቁን የትግራይ ሪፐብሊክ መመስረት ግብ አድርጎ መመስረቱና ለዚህም አላማው ስኬት የቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ እንድሚገኝ የሚታወቅ ነገር ነው።
በተለይም በወልቃይት፣ ፀገዴና አርማጭሆ ያካሄደው መስፋፍት በአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ላይ ትውልድ ይቅር የማይለው ግፍ ፈጽሟል፡ አሁንም የመስፋፋት ህልሙን እውን ለማድረግና ቀሪ የአማራን መሬት ለመቆጣጠር ያለማቁአረጥ ጥረት እያደረገ ነው። ከላይ በተጠቀሱት አካባቢወች የሚኖረውን የአማራን ህዝብ በማንበርከክ እኩይ ፍላጎቱን ለማስፈፀም ቀደም ሲል የጎንደር አስተዳደር ከተሞች በነበሩና አሁን በጉልበት ወደ ትግራይ በተወሰዱ ሁመራ፣ ማይካድራ፣ ማይፀብሬ፡ ዳንሻ፣ ማክሰኞ ገበያ/ ንጉስ ከተማ/ና ዲቪዥን የተባሉ ከተሞችን ማዕከል
በማድረግ በአካባቢው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችን በተለይም ምልስ የህወኃት ወታደሮችን በመመልመል ከሃምሌ 2006 እስከ መስከረም 2007 ለሶስት ወር የዘለቀ በሁመራ ከተማ ለ120 ሰወች ልዩ የስለላና የአፈና ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን በፀለምት ዲቪዥን ከተማና በዳንሻ ከተማ በያንዳንዳቸው 1500 የሰው ሃይል ለፀጥታ ስራ በሚሊሻነት አሰልጥኗል። በተጨማሪም በማይካድራና ንጉስ ከተሞች በያንዳንዳቸው 1000 የሰው ሃይል ለተመሳሳይ አላማ አሰልጥኗል። በአጠቃላይ ተከዜን ተሻግረው ከሚኖሩት ትግሬወች 5120 ተመልምለው ለሶስት ወር የዘለቀ ስልጠና ወስደው መደበኛ ደመወዝም ተመድቦላቸው ለተጨማሪ የመስፋፋት አላማቸው አዝጋጅተው አሰማርተው እንደነበር በወቅቱም ታውቆ ነበር። እነዚህ ለአፈናና ለግድያ የሰለጠኑ ሃይሎች አሁንም ተደራጅተው ለህወኃት እየሰሩ ያሉ ናቸው።


ይህንኑ ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ ከባለፈው ታህሳስ 17 ጀምረው በርካታ የፀጥታ ሃይል ከሌሎች አካባቢወም በመጨመር ህወኃት በሰሜናዊ ምዕራብ ጎንደር ላይ ሰፊ የመስፋፋት ዘመቻ ከፍቶ እንደነበረና በአካባቢው ህዝብ የተደራጀ ትግል ያሰበውን ሳያሳካ መቅረቱ ይታወሳል። ድርጅታችን የአማራ ዴሞራሲያዊ ሃይል ንቅናቄም ከህዝቡ ጎን በመሰልፍ ተስፋፊውን የህወኃት ቅጥረኛን ከመፋለምም በተጨማሪ ወቅታዊ መረጃወችንም ለህዝብ በማድረስ ወሳን ሚናውን ተወትቷል ፣ አሁንም እየተወጣ ይገኛል።


ህወኃት ያሰበውን የቅዠት ህልሙን ለማሳካት የጀመረው መንገድ ከአካባቢው ህዝብ ባጋጠመው ተቀዋውሞና ትግል ትልቅ ፈተና እንደገጠመው ስላወቀ አላማውን ለማሳካት በአሁኑ ሰዓት ሁለት አይነት ዘዴወችን ቀይሷል።


1ኛ. የፌደራል መንግስቱ ጣልቃ ገብቶ እንዲወስን በማድረግ አካባቢውን መቆጣጠር ነው፣ ለዚህም ጥር 04/05/07 ፀገዴ ወረዳ ማክሰኞ ገበያ ከተማ ላይ ከፀገዴና አካባቢው ህዝብ ጋር ትልቅ ስብሰባ ተካሂዷል። በስብሰባው የተገኙ 1, ዶ/ር ሽፈራው ተክለማሪያም 2. አባይ ወልዱ 3. ተወድሮስ ሃጎስ 4. ገዱ አንዳርጋቸው 5. ሌ/ጅ ብርሃኑ ጁላ /የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ/ 6. ሜ/ጅ ገብረግዛብሄር መብራቱ /የመከላከያ ዘመቻ ሃላፊ/ እና ሌሎችም ነበሩ። በዚህ ስብሰባ ህዝቡ በአንድ ቃል እኛ አማራ ነን እንጅ ትግሬ አይደለንም የትግሬና የጎንደር ደንበር ተከዜ ነው ትግሬ ተከዜን ተሻግሮ ግዛት ሊኖረው አይገባም በሚል ቁጣ ባዘለ መልኩ ነግሯቸዋል። ህወኃቶቹ እነ አባይ ወልዱም በሁኔታው መበሳጨታቸው የታወቀ ሲሆን የደላንታው ተወላጅ ገዱ አንዳርጋቸው ህዝቡ ያነሳውን እና ያራመደውን ሃሳብ ደግፏል፡ የህዝቡን ውሳኔ ማክበር አለብን በማለት ከህወኃቶች ጋር ትልቅ ልዩነት መፍጠሩ ሲታወቅ፣ መግባባት ባለመቻላቸው ጉዳዩን ፌደራል ጣልቃ ገብቶ ይይልን ሲሉ ህወኃቶች ባቀረቡት ሃሳብ ተግባብተው ስብሰባው ተጠናቁአል። አሁን አካባቢው ብዙ የፌደራል የፀጥታ ሃይል የተከማቸበት ሲሆን ከፌደራል መንግስቱም የሚጠበቅ ነገር ስለለለ ህዝቡ ለነፃነቱ ለሚያደርገው ትግል በተለየ መንገድ እየተዘጋጀ ሲሆን ድርጅታችንም ይህንኑ በማጠናከር ትኩረት አድርጉኣል።


2ኛ. በጎንደር ክ/ሃገር የሚኖሩ የቅማንት ማህበረሰብን የማይገባ የፈጠራና ልብወለድ ታሪክ በመንገርና አንዳንዶቹንም በጥቅም በማታለልና በማሳሳት በፀረ-አማራነት እንዲሰለፉ እያደረገ ነው። ይህ ተንኮል ቀደም ብሎ ጀምሮ በደንብ ታስቦበት ሲሰራበት እንደቆየ ሁኔታውን በቅርብ የሚከታተሉ ሃይሎች ያውቁታል። ህወኃት አሁን ላይ የገንዘብና የስልጣን አቅሙን በመጠቀም የቅማንት ማህበረሰብን ዘራችሁ ከትግሬ እንጅ ከአማራ አይደለም መጀመሪያ የራሳችሁን አስተዳደር መስርቱና የራስን ኣድል በራስ የመወሰን መብታችሁን ተጠቅማችሁ ወደ ዘራችሁ ወደ ትግራይ ትካለላላችሁ በማለት የመስፋፋት ህልሙን እውን ለማድረግ በሌላ መንገድ ተግቶ እየሰራ ነው።


ሁኔታው የሚመለከታችሁ ወገኖቻችን ሁሉ ይህ በጎንደር ነዋሪ ህዝብ ላይ እየተካሄደ ያለው ግፍና በደል የጎንደር ብቻ ሳይሆን የአማራው የጋራ ጥቃትና የኢትዮጵያዊያንም በደል ነው። ስለሆነም በጉዳዩ ላይ መነጋገርና በመፍትሄው ላይም መተባበር የሁላችንም ግዴታ እንዲሆን ያስፈልጋል።

- See more at: http://satenaw.com/amharic/?p=4115#sthash.nE9aWRYK.dpuf

No comments:

Post a Comment