Wednesday, January 7, 2015

የማለዳ ወግ … ሰሚ እስኪገኝ እያነባን እንጮሃለን ! – ነቢዩ ሲራክ

የማለዳ ወግ … አፈ ጉባኤ አባ ዱላ …ግን ለምን አልሰሙንም ?* የኮንትራት ሰራተኛዋ አይነ ብርሃኗን ማጣትና የስም የለሿ ሟች እህት መጨረሻ   !
*  ሰሚ እስኪገኝ እንጮሃለን  !

  ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓም ሰኞ በማለዳው ያገኘኋቸው ሁለት መረጃዎች የወጡት በሁለቱ አንጋፋ የሳውዲ ጋዜጦች በአረብ ኒውስ Arab News  እና በሳውዲ ጋዜት Saudi Gazette  ነው ። በአንዱን አይቸ ቢከፋኝ ፣  መፍትሔ ላይገኝ ይህን መርዶ ከንፈር ለማመስመጠጥ  ብቻ መረጃ ብየ ልለጥፍ ይሆን ?  እያልኩ ከራሴ ጋር ሙግት ገጥሜ ነፍሴን ሳስጨንቀት በሌላኛው ጋዜጣ የወጣውን ሌላ መረጃ አንድ ወዳጀ በጓዳው የመልዕክት መሰረጫ እንደኔው ማልዶ ያጋጠመውን የወገን መከራ አደረሰኝ ። ሁለቱንም አሳዛኝ መረጃዎች ተመለከትኳቸው ፣ ያማል ብቻ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም  !



ከሳምንት በፊት እኔ ከምኖርበት ጅዳ ከተማ ልጆችን ወደ ት/ቤት በማድረስ ላይ እያለች በተፈጠረ መኪና ግጭት የያዘቻቸውን ህጻናት አትርጋ እሷ መስዋዕትነት የከፈለችን ትጉህ እህት ያዩ አረቦች ተገርመው በምትሰራበት ቢተ ሲጫወቱ የሰማች እህት ታሩኩን በደፈናው ብትነግረኝም ዝርዝር መረጃ አለነበረውምና በዝምታ አልፊው ነበር።  ዛሬ እኩለቀን ላይ ከላይ የጻፍኩትን የሁለቱን ጋዜጦች መረጃ የተመለከተ ወንድም አንዲህ የሚል መልዕክት ደረሰኝ ይህን “ሄሎ ነብዩ ሰላም ነህ ነብዩ በአንድ ጉዳይ ፈልጌህ ነበር
ስልክህን  ልትልክልኝ በትህትና እጠይቃለህ በጣም የማከብሪህ  እና ማደንቅህ …” ይላል ፣ አመስግኘ ስልኬን ሰጠሁት ፣ ምሽቱን ደውሎልኝ ከባድ የመኪና አደጋ ደርሶባት ራሷን የማታውቀውን እህት ጉዳይ አንስቶ በዝርዝር አጫወተኝ ፣ ይህች እህት ያን ሰሞን የአሰሪዎቿን ልጆች አትርፋ መኪናው የዳጣት ለመሆኗ ብዙ መሄድ አላስፈለገኝ። ከወዳጀ ጋር ይህችን ምንዱብ የአልጋ ቁራኛ ለማየት ቀጠሮ ብንይዝም አልስቻለኝምና ወደ ተባለው ሆስፒታል ሄጀ የማትሰማ የማትናገረውን እህት አይቻት ሰላሜን በገዛ እጀ አጥቸ ተመለስኩ  !ግን ለምን አልሰሙንም ?የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በሳውዲ አረቢያ ጉብኝት አድርገዋል። የሰራተኛ ሚኒስትር አድል ፈቂን ጨምሮ በርካታ የመንግስ ሃላፊዎች አግኝተው እኔና መሰሎቸ ሌት ተቀን ስለምንናገረው በቂ ዝግጅት ሳይደረግ ስለተላኩ የእኛ ዜጎች ለአባ ዱላ ነግረውልናል ።  አፈ ጉባኤ አባ ዱላ በኮንትራት ሰራተኞች ጉዳይ ከሳውዲዎችና መብታችን ካላስጠበቁልን የሪያድ ኢንባሲና የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ፣ በሃላፊዎች  ከተመረጡ  የሪያድ የጅዳ “የተከበሩ ምርጥ” ዜጎች ፣  ከኢህአዴግ የድርጅትና ከተለያዩ ጥሪ ከተደረገላቸው የ ማህበር አባላት ጋር  መክረዋል።

አፈ ጉባኤውና ልዑካኑ በአንጻሩ በማህበራዊ ኑሮው ፣ በመብት ጥበቃው ፣ በኮንትራት ሰራተ ኞች የለት ተለት የመረረ እውነት ተመልካችና ገፋች የሆነውን ነዋሪ ጠርተው ቀርቶ ሊያይ ሊያነጋገራቸው ሄዶ በሆድ አደር አጋፋሪዎች ተከልክሏል። ነዋሪ ዜጋው እንዲህ ተገፍቶ  የሃገሪቱ የበላይ ህግ አውጭ የሆነው የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሳያዩትና ሳያነጋግሩት ሔደዋል ። የአፈ ጉባኤ አባ ዱላን ማግኘትና ብሶቱን ማሰማት የፈለገው ነዋሪ ጉጉት ምን ይሆን ? ብየ ጠያይቄም ነበር ። ያገኘሁት የምላሽ እውነታ ነዋሪው ማቆሚያ ስለጠፋው የኮንትራት ሰራተኞች አበሳ ለመናገር መተንፈስ እንጅ መጓጓቱ መፍትሔ ከባለስልጣኑ ይገኛል ብሎ አለመሆኑን ተረድቻለሁ።  እውነት ነው አባቶች  ” ድሃ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ… ” እንደሚሉት ሆነና  ነዋሪው ሆየ ብሶቱን ማሰማቱ ህመሙን ያቀልለት መስሎታል  ! ፕሬዚደንትና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ እስካሁን ሳውዲ ለመጡት ከፍተኛ ባለስልጣኖች የአለ የሌለ የተባለውን ጥያቄ አቅርቦ ምልስ እንዳልተገኘ አሳምሮ የሚያውቀው ነዋሪ በዚህና በዚያ ተስፋ  ቆርጧል… ግን ተስፋ ቆርጦም መናገር መተንፈስ ይፈልጋል !

የአስፈሪው ቀን መቅረብ  ምልክቶች …

በሳውዲ መንግስት የተዘጋው የኮንትራት ሰራተኞች ይጀመራል ተብሎ በዋና ዋና ደላሎች ወሬው ከተነዛ ወዲህ በመንግስት በኩል የረቂቅ ደንቡ መውጣቱን ሰምተናል ። ጸድቆ ጉዞው ሊጀመር ተቃረበ ሲሉን ደግሞ አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ ከሳውዲ ባለስልጣነናት ጋር ስለአዲሱ ረቂቅ ህግ መምከራቸውን ሰምተናል ! ከሳውዲዎች ጋር   ስለመከሩ ስለዘከሩበት ህግ በሳውዲ ነዋሪ ከሆነው ኢትዮጵያዊ ጋር አለመምከራቸው ግን ታላቅ ታሪካዊ ስህተት ነው ባይ ብዙ ነን  !  ነዋሪው ብሶቱን ለመናገርም ሆነ ከመምከር መወያየቱ የሚገኝ ፋይዳ አለ ብሎ ሳይሆን እንደ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ ባለ ስልጣን ለምን ዜጎችን እኩል አይተው አላነጋገሩንም ? ሃሳባችን ለምን አያደምጡትም? ለምን አልሰሙንም ?  ለምን የታመቀ ችግራችን ቢያንስ አላዳመጡንም  ? በኦሮሞ ልማት የተመረጡ አባላት ሰብስበው ለቴሌቶን ብር ከመሰብሰብ በስደት ስላለው ስለከፋው ዜጋ መምከር ለምን አለቀደመም?   አፈ ጉባኤ አባ ዱላ  እንደ ኢትዮጵያ የተወካዮች ምክር ቤት ሳውዲን እየጎበኙ ለምን ወደ ዘውግ አድልተው ወርደው ጊዜን ማባከብ አስፈለጋቸው? በጉብኝታቸው ሁሉንም ባንድ የኢትዮጵያ ባንዴራ ማሰተባሰበርና ማመካከር ሲገባ ቅድሚያ ለኦሮሞ ማህበር ከዚያን የኢህአዴግ አደረጃጀት እያሉ ስደተኛውን ከመበታተንና በማዕከላዊነት ያልተማከለ ፣በዘውግ አስተዳደር የከረረ  አካሄድን እንድናይ ለምን አደረጉ?   አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ከምንም በላይ በሁለት ሃገራት የሰራተኛ ውል ማዕቀፍ ውጭ ወደ ሳውዲ የመጡና  እንደ ጨው የተበተኑትን የኦሮሞ ፣የአማራ፣ የትግራይ ፣ የጉራጌ እና የቀሩትን ብሔረሰቦች የአብራክ ክፋዮች ሁኔታ ለመረዳት የጉዳዩ ባለቤትና መከራውን ገፋች ነዋሪውን አላነጋገሩትም።  መፍትሔው  መብታችን ማስከበር ቀርቶ ዜጎች ያለንበትን ሁኔታ መሸፋፈን ከሚቀናቸው ከቆንስልና ከኢንባሲ ተወካዮች እስከ ድርጅትና ማህበራት ያሉትን”ምርጥ ” የተባሉ ነዋሪዎች ማነጋገር መፍትሔ ነውን ?  አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ነዋሪውን በነቂስ ጠርተው በመሰብሰብ ለምን ስለመጡበት ጉዳይ ማብራሪያም ሆነ የነዋሪውን ሃሳብ አልወሰዱም ?  የሚሉ በርካታ ውሃ የሚያነሱ እውነት ያላቸው ጥያቄዎችን ነዋሪው ሲያሰማ አድምጫለሁ ! እኔም ሆንኩ ነዋሪው በእስካሁኑ ሂደት ያየነው ለውጥ ኑሮ ባያስደስተንም ባለስልጣን በመጣ በሄደ ቁጥር ድመጻችን ይሰማ ዘንድ እንሻለን ፣   የለውጥ ተስፋ ባይታየንም የወገናችን አበሳ ግን መናገር አናቆምም  ! አዎ  ! ሰሚ እስክናገኝ እንጮሃለን  !

እስኪ ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓም

- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/3328#sthash.tRTfH1mV.dpuf

No comments:

Post a Comment