Wednesday, January 28, 2015

(ሰበር ዜና) አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት መዛወራቸው ተሰማ

(ዘ-ሐበሻ) የመን ላይ በሕወሓት አስተዳደር ታግተው ኢትዮጵያ ከገቡ በኋላ እስካሁን የትኛው እስር ቤት ታስረው እንደነበር የማይታወቁት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቃሊቲ እስር ቤት መዘዋወራቸው ተሰማ::

ምንጮች ለዘ-ሐበሻ እንዳስታወቁት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በቃሊቲ እስር ቤት ቀድሞ ስዬ አብርሃ የታሰሩበት ክፍል ታስረዋል::

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላለፉት 6 ወራት የት እንዳታሰሩ የማይታወቅና የብዙ ሕዝብ ጥያቄ የነበረ ሲሆን ከሳምንታት በፊት ከማይታወቀው እስር ቤት ከባለቤታቸው ጋር ማውራታቸውና ለልጆቻቸውም ያልሆነ ተስፋ እንደማይሰጡ መናገራቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል::

በተለይም ሰሞኑን የ እንግሊዝ ፓርላማ አባላት ወደ አዲስ አበባ በአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ለመነጋገር እንደሚሄዱ ከተነገረ በኋላ አቶ አንዳርጋቸው ወደ ቃሊቲ እስር ቤት መዘዋወራቸው አነጋጋሪ ሆኗል:: አቶ አንዳርጋቸው ለሕዝብ ክፍት ሆነው እንዲጠየቁ የሕወሓት አስተዳደር ይፍቀድ አይፍቀድ የታወቀ ነገር የለም::


No comments:

Post a Comment