Thursday, January 22, 2015

በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር በተቃዎሟቸው ኢትዮጰያውያን ላይ የመሰረቱትን ክስ የስዊድን ፖሊስ ውድቅ አደረገው።

ጥር ፲፬(አስራ አራት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀደም ሲል የኢህአዴግ መንግስት ፤ በስዊድን-ስቶኮሆልም አዘጋጅቶት የነበረው የቦንድ ሽያጭ ዝግጅት ላይ ኢትዮጰያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወቃል።
<<ከአባይ በፊት ዘረኝነት ይገደብ>> በሚል መርህ ተቃውሞውን ያደረጉት ኢትዮጰያውያን፤ ዜጎች ያለፍርድ እየታሰሩና እየተገደሉ ባለበት ሁኔታ ገንዘብ ለመሰብሰብ መሯሯጥ፤ በሀገርና በህዝብ ላይ መቀለድ እንደሆነ በመናገር ነበር- ተቃውሟቸውን ጫማና እንቁላል በመወርወር የገለጹት።
ኢትዮጰያውያኑ -አምባሳደሯን መኪና ላይ የ እንቁላል መዓት በመወርወር ተቃውሟቸውን ሲገልጹ፤አምባሳደር ወይንሽት ከመኪናቸው መውጣት ተስኗቸው ተስተውለዋል። በኦትዮጰያውያኑ ጫማና እንቁላል የተወረወረባቸው በስዊድን የኢትዮጰያ አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ፤ <<ስራዬን መስራት እስከማልችል ድረስ በደል ደርሶብኛል>> በማለት ለስዊድን ፖሊስ ክስ ይመሰርታሉ።
የአምባሰደሯን ክስ ተከትሎ የስዊድን ፖሊስ ባቀረበላቸው ጥሪ መሰረት ቃል ለመስጠት የሄዱት የኢትዮ-ስዊድን ግብረ-ሀይል አስተባባሪ አክቲቪስት መቅደስ ወርቁ እና የኢትዮጰያ ዲሞክራቲክ መድረክ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ሞላ፤ ኢትዮጰያ ውስጥ ስላለው የመብት ረገጣና በስፋት ለስዊድን ፖሊስ በማብራራት፤ ተቃውሞው የተደረገው የሰብዓዊ መብት ጥሰትን፣ዘረኝነትን እና ሙስናን ለመቃወም እንደሆነ አስረድተዋል።
ጉዳዩን የተመለከተው የስዊድን ፖሊስም በስዊድን ህግ መሰረት የዚህ ዓይነት ተቃውሞ ማድረግ መብት እንጂ ወንጀል እንዳልሆነ በመጥቀስ እና ክሱ ውደ ፍርድ ቤት የሚያመራበት አንዳችም የህግ ምክንያት እንደሌለ በማብራራት የአምባሰደሯን ክስ ውድቅ እንዳደረገው አክቲቪስት መቅደስ ተናግረዋል። የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ከወራት በፊት በዋሽንግተን ዲሲ የልብስ መደብር ውስጥተቃውሞ ባቀረቡባቸው አክቲቪስቶች ላይ የመሰረቱት ክስ ሰሞኑን በአሜሪካ ፍርድ ቤት ውድቅ መደረጉ ይታወቃል።


No comments:

Post a Comment