Thursday, May 19, 2016

በኦሮምያ ህዝባዊው ተቃውሞው አገረሸ

ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለሳምንታት ጋብ ብሎ የነበረው የኦሮምያ ክልል ተቃውሞ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መጠነኑን እያሰፋ በመምጣት ላይ ሲሆን፣ ዛሬ በምእራብ ሃረርጌ የማሳለ ከተማ ነዋሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ አሰምተዋል። ከሁለት ቀናት በፊት በአሰቦ ከተማ ተመሳሳይ ተቃውሞ የተካሄደ ሲሆን፣ ትናንት ምሽት ደግሞ በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የፈደራል ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ እርምጃ ወስደዋል። በርካታ ተማሪዎችም መጎዳታቸው ታወቋል።

መንግስት የአዲስ አበባ አዲሱን ማስተር ፕላን መተውን በይፋ ካስታወቀ በሁዋላ፣ የአርሶ አደሩን መሬት መልሶ የሚወስድበትን አዲስ እቅድ ይፋ አድርጓል። እቅዱን አርሶ አደሮች አጥብቀው በመቃወም ላይ ናቸው።

No comments:

Post a Comment