Monday, May 16, 2016

አሸዋ ሜዳ በሚባለው አካባቢ የተገነቡት የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ሙሉ በሙሉ ለኢህአዴግ ካድሬዎች ተሰጡ

ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እሁድ ግንቦት7፣ 2008 ዓም በኦሮምያ ልዩ ዞን ወደ አምቦ መስመር መውጫ አሻዋ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተገነቡት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ሙሉ በሙሉ ለኢህአዴግ ባለስልጣናትና ካድሬዎች መሰጠቱን ወኪላችን ገልጿል። ቤቶቹ ከተገነቡ ብዙ አመታትን ማስቆጠራቸውን የገለጸው ወኪላችን፣ በቅርቡ በተካሄደው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ቆጠራ ይህ አካባቢ መተላለፉን ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። እነዚሁ የመንግስት ባለስልጣናትና ካድሬዎች የተሰጣቸውን ቤት ከ2 እስከ 3ሺ ብር እያከራዩ ተጨማሪ ገቢ ያገኛሉ።

ባለፈው ሳምንት የከተማ ቤቶችና ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያው ሃይሌ በቅርቡ በተደረገው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ቆጠራ 4 177 ቤቶች ጥቅም ላይ ሳይውሉ መገኘታቸውን የተናገሩ ሲሆን፣ 286 የኢህአዴግ ባለስልጣናት የተሰጣቸውን ቤቶች ለሶስተኛ ወገን አከራይተው ገቢ እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment