Tuesday, May 3, 2016

10 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአራት ወራት ጊዜያት ውስጥ ተዘጉ።

ሚያዚያ ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ኤጀንሲ የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው የውጭ ጉዲፈቻ ድርጅቶችን ጨምሮ የአለምአቀፍና የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች በዋንኛነት በፋይናነንስ ችግር ምክንያት መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው

ተዘግተዋል። እነዚህም ድርጅቶች ኤልሮኢ አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት ፖዘቲቨ ውሜን ማህበር፣ አዶፕትስ ጆንስ ፍረም፣ ሄይነሪች ቦል ፋውንዴሽን፣ ካናዲያን አድቮኬት ፎር ዘአዶፕሽን ኦፍ ችልድረን፣ ሴኬም የልማት ድርጅት፣ ለውጥ በህብረት የተቀናጀ የማህበረሰብ ስልጠና ልማት ማህበር፣ ሊቪንግ ሆፕ ውመን ኦርጋናይዜሽን፣ ፖይዲያ፣ ፊዩቸር ግሩፕ ግሎባል አውትሪች ኢንክ፣ ህብረተሰብ አቀፍ ልማት ድርጅት ናቸው።

ኤጀንሲው በተዘጉት ድርጅቶች ላይ የመብት ወይም የእዳ ጥያቄ ያላቸው በ15 ቀናት ጊዜያት ውስጥ እንዲቀርቡ በአዲስዘመን ጋዜጣ ይፋዊ ማስታወቂያ አውጥቶአል።
ከኤጀንሲው በተገኘ መረጃ መሰረት እ ኤ አ ከ2009 እስከ 2012 ባሉት ጊዜያት ብቻ 2ሺ 709 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በፌዴራል ደረጃ ተመዝግበዋል። እነዚህ ድርጅቶች የሀገሪቱን የውጭ ንግድ አመታዊ ገቢ በአራት እጥፍ የሚልቅ ወደ 12 ቢሊየን ዶላር በአመት ያንቀሳቅሳሉ። ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ምርጫ 97 ን ተከትሎ ባወጣው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች አፋኝ ህግ ምክንያት ብዙዎቹ ድርጅቶች እንቅስቃሴያቸው መዳከሙ የመንግስትን
ትልቁ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ እንዲነጥፍ ከማድረጉ በተጨማሪ ፣ ድርጅቶቹም ቀስ በቀስ እየተዘጉ በመምጣታቸው ምክንያት የያዙት ሰፊ የሰው ሀይል ወደስራ አጥነት እየተቀየረ መምጣቱ በመታየት ላይ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል።

No comments:

Post a Comment