Tuesday, May 31, 2016

መንግስት በአንድ ወር ውስጥ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና እንደሚያዘጋጅ አስታወቀ

ግንቦት (ሃያ ሦስ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና  አስቀድሞ መውጣቱን ተከትሎ የፈተናውን መሰረዝ በተምታታ መግለጫ ያወጀው መንግስት፣ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አፋጣኝ የሆነ ፈተና እንደሚሰጥ አስታውቋል። ፈተናው ከሰኔ 27-30 እንደሚሰጥ የተገለጸ ቢሆንም፣ ሰኔ 28 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የኢድ አል ፈጥር በአልን የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ በተማሪዎች ላይ የሚያመጣው ተጽእኖ ቀላል አይሆንም በማለት ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ነው።

ፈተናው እንዴት ወጣ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ እያጣራሁ ነው ያለው መንግስት፣ ባለሙያዎቹ ተፈታኝ የስጋ ዘመዶች እንደሌላቸው የማረጋገጡ ስራ በጥንቃቄ ይሰራል ሲል ዘመዶች ያሉዋቸው ፈተና አውጪዎች ፈተናውን እንዳወጡት ፍንጭ ለመስጠት ሞክሯል። የኦሮሞ አክቲቪስቶች  በበኩላቸው ፈተናው እንዲሰረዝ ያደረግነው እኛ ነን በማለት እየተናገሩ ነው። ይህን እርምጃ የወሰዱትም በመንግስት ላይ ተቃውሞ ሲያቀርቡ የነበሩ ተማሪዎች ያለ በቂ ዝግጅት እንዲፈተኑ መደረጉ አግባብ ባለመሆኑ ነው ይላሉ። መንግስት እነዚህ ወገኖች ለሚያቀርቡት አስተያየት መልስ አልሰጠም።

No comments:

Post a Comment