Sunday, September 27, 2015

ጦላይ የሰለጠኑ የሕወሓት ደህንነቶች ወደየመጡበት አህጉር ተላኩ::

ምኒሊክ ሳልሳዊ  በሕወሓት ተመልምለው ከውጪው አለም የሚኖሩ ዲያስፖራ የሕወሓት ደጋፊዎች የደህንነት እና ስለላ ስራዎችን ስልጠና በጦላይ ከጨረሱ በኋላ ወደየመጡበት አህጉር መመለሳቸው ምንጮች ጠቁመዋል::ከሰሜን አሜሪካ አውሮፓ እና መካከለኛ ምስራቅ እንዲሁም ከአፍሪካ ተመልምለው የመጡ እና በስራ ፈትነት በዲያስፖራው መሃል ሲኖሩ የነበሩ የሕወሃት ደጋፊ ዲያስፖራዎች የደህንነት እና ስለላ ስልጠና ለአንድ አመት ከስድስት ወር በኋላ ከተከታተሉ በኋላ ወደየመጡበት ተመልሰው ለስራ እንደተላኩ ታውቋል::

በዲያስፖራው መሃል ተሰግስገው የጥላቻ እና የጠባብነት መርዝ ለመርጨት እንዲሁም ሰርገው በመግባት የዲያስፖራውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለመሰለል በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች በየሃገሩ የሚያደርጉትን የቢዝነስ እንቅስቃሴ እና ሌሎች ስራዎችን በተመለከተ እንዲያጠኑ እና ሪፖርት እንደሚያደርጉ ታውቋል::የወያኔው ጉጅሌ መንግስት በዲፕሎማሲው መስክ የተለያዩ የበለጸጉ ሃገራትን በብሄራዊ ጥቅማቸው በመያዝ ዜጎችን ለብሄራዊ ውርደት በመዳረግ በምእራባውያን ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ተቀባይነት አለው::ቢሆንም አብዛኛው ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ለአገዛዙ ከፍተኛ ጥላቻ ስላላቸው ድጋፋቸውን መንፈጋቸው በአባይ ቦንድ ሽያጭና በተለያዩ አጋጣሚዎች ያላቸውን ተቃውሞ ማሳየታቸው ይታወቃል::

No comments:

Post a Comment