Thursday, September 3, 2015

በከባድ መኪና ውስጥ ተደብቀው ሲጓዙ የነበሩ መቶ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በዛምቢያ ፖሊስ ተያዙ

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስደተኞቹን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ከባድ መኪና በናካንዳ የድንበር የፍተሻ ጣቢያ አቅራቢያ ፓሊስ የደረሰውን ጥቆማ ተከትሎ ተይዘዋል።

ሕገወጥ ስደተኞችን በማዘዋወር ሲሰሩ የነበሩ ሶስት የዛንቢያ ዜጎችም አብረው ተይዘዋል። ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከአስር እስከ ሃምሳ ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ። ስደተኞቹ በአሁኑ ወቅት በኳቤ የደኅንነት እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙና የከባድ መኪናውን የመጨረሻ መዳረሻ ለማወቅ የፀጥታ ሰራተኞች ምርምራቸውን መቀጠላቸውን ዛንቢያ ዴሊ ኔሽን ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment