Friday, September 18, 2015

በኮንጎ ብራዛቪል ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ድል እየቀናቸው ነው

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኮንጎ ብራዛቪል አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው በመላው የአፍሪካዊያን ጫወታ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ድል እየቀናቸው ነው።

በ5 ሺ ሜትር የወንዶች የሩጫ ውድድር ጌትነት ሞላ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያገኝ፣ ርቀቱን በ 13 ደቂቃ 21 ሰከንድ 88 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል። ልዑልሲ ገብረስላሴ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።
በ1 ሺ500 ሜትር የሴቶች የሩጫ ውድድርም ኢትዮጵያዊያን ሯጮች በድጋሚ ድል ቀንቷዋቸዋል።
ዳዊት ስዩም 4 ደቂቃ 16 ሰኮንድ 69 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ርቀቱን በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ስትሆን ፣ ሌላዋ ሯጭ በሶ ሳዶ ደግሞ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

No comments:

Post a Comment