Monday, September 7, 2015

የአርበኞች ግንቦት ፯ በተለያዩ ከተሞች ያካሄደው የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደት የተሳካ የህዝብ ስብሰባ ማካሄዱን አመልክተዋል።


1eac1-pg7-logoባሳለፍነው ሳምንት የአርበኞች ግንቦት ፯ በተለያዩ ከተሞች ያካሄደው የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደት የተሳካ የህዝብ ስብሰባ ማካሄዱን ከየስፍራው የደረሰን ሪፖርቶች አመልክተዋል።
ቅዳሜ እና እሁድ በካናዳ ካልጋሪ ፣ቶሮንቶ ፤ በአሜሪካን ኦክላንድ ካሊፎርኒያ እንዲሁም በአዉሮፖ ኖርዌይ፣ ሲዉዘርላንድ የተዘጋጀው ህዝባዊ ስብሰባ ታሪካዊና የትግል መነሳሳት የታየበት እንደነበር ታውቋል።
በአሜሪካን ሀገር አቶ ቸኮል ጌታሁን ፣ በካናዳ አቶ አበበ ቦጋለ እና በአዉሮፓ አቶ ብዙነህ ፅጌ በየስብሰባው ተገኝተው የኢትዮጵያ ህዝብ የተጀመረውን እልህ አስጨራሽ የነፃነት ትግሉን መደገፉ አለበት ብለዋል።
በየከተማው የሚደረገው የህዝብ ተሳትፎ የሚደነቅ እና የሚበረታታ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በእነዚህ ከተሞች ሁሉ ቁጥሩ በርካታ የሆነ ህዝብ የተሳተፈ ሲሆን፤ በሚሊየን የሚቆጠር ብርም ተሰብስቦል።
ትግሉ ዳር እስኪደርስ ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉት የገንዘብ ቁሳቁስ ድጋፍ እንደማይቆረጥ ቃል ገብተዋል።

No comments:

Post a Comment