Wednesday, September 30, 2015

በሳውድ አረቢያ በሃጅ ጸሎት በተፈጠረ መጨናነቅ የተነሳ የሞቱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በውል አልታወቀም

መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እስካሁን 13 ሰዎች እንደሞቱ ቢገልጽም፣ የመጨረሻው መረጃ ይፋ ሲሆን ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊልቅ ይችላል።

ከአስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ሼህ አህመድ ከሳውድ አረቢያ እንደገለጹት፣ 13 ቱ ሟቾች የተለዩት ዘመዶቻቸው ባረጋገጡት መሰረት ነው።

የሳውዲ መንግስት የሟቾችን ቁጥር ሙሉ በሙሉ ለማሳወቅ እንዳልቻለ የገለጹት ሼህ ሙሃመድ፣ ከዚህ ቀደም ከክሬን መውደቅ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን አደጋ ተከትሎ የተፈጠረ በመሆኑ፣ ችግሩን እንዳወሳሰበው ገልጸዋል። መንግስት የመጨረሻውን መረጃ ይፋ ሲያደርግ የሟቾች ቁጥር ከተጠቀሰውም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ይጠበቃል።
ከፍተኛ እልቂት ካጋጠማቸው የአፍሪካ አገራት መካከል ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ ናይጀሪያ፣ ማሊ፣ ኒጀርና ካሜሮን ይጠቀሳሉ። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር መንግስት ከገለጸው በብዙ እጥፈር ሊጨምር ይችላል በማለት የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎችን እያቀረቡ ነው። ዋናዋ የሳውዲ መንግስት ባላንጣ የሆነቸው ኢራን ፣ የአገሪቱ መንግስት ይቅርታ እንዲጠይቅ እና ለተጎጂዎችም አስፈላጊውን ካሳ እንዲከፍል እየወተወተች ነው።

No comments:

Post a Comment