Monday, September 7, 2015

አልሸባብ ሁለተኛዋን ስትራቴጂክ ከተማ ተቆጣጠረ

ጷግሜን ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ የአፍሪክ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም በኡጋንዳና በኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥጥር ስር የነበረው በመሃከላዊ ሂራን ግዛት ቡቅአበል ሁለተኛው ስትራቴጂካዊ ከተማ በአልሸባብ ቁጥጥር ስር ውሏል።

እስላማዊ ታጣቂዎቹ በስተደቡብ ሶማሊያ የምትገኘውን ኩርቱዋሬንና ከሞቃዲሾ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘውን የጃናሌን ከተሞች ባለፈው ሶስት ቀናት በቁጥጥራቸው ስር ማድረጋቸው ይታወሳል።
በሶማሊያ ከ6,200 በላይ የሚሆኑ የኡጋንዳ ወታደሮች የሚገኙ ሲሆን የኡጋንዳ መንግስት በጦርነቱ 12 የሰራዊቱ አባላት መገደላቸውን ቢናገርም ገለልተኛ የሆኑ የውጪ የዜና አውታሮች ግን ቁጥሩን ከ50 በላይ መገደላቸውንና ከ50በላይ የሚሆኑት ያሉበት እንደማይታወቅ ገልፀዋል።
ለቡሉንበርግ የዜና አገልግሎት አንድ የአካባቢው ነዋሪ በስልክ እንደገለፁት ብዛት ያላቸው ጭንብል ያጠለቁ የአልሸባብ ሚኒሻዎች ከተማዋን ተቆጣጥረዋታል። ሲሉ እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮችም የበደወይኔን ከተማ በመልቀቅ 90ኪሎሜትር ላይ ሰፍረዋል። ሲሉ የሶማሊያ የጦር ኃላፊ አስረድተዋል። የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም አልሸባብን ሙሉ ለሙሉ የመደምሰስ ዘመቻ መክፈታቸው ሲነገር ቢቆይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ዳግም አልሸባብ በማንሰራራት ጥቃት መሰንዘሩን ቀጥሎበታል።
የኡጋንዳው ሰንደይ ሞኒተር ጋዜጣ እንደዘገበው የኡጋንዳ ወታደሮች የዘጠኝ ወራት ደመወዛቸው እንዳልተከፈላቸው ገልፆ በዚህ ምክንያት ሰራዊቱ የሞራል ውድቀት ውስጥ እንደገባ ሜይል ዘጋርዲያን አፍሪካ አክሎ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment