Thursday, September 10, 2015

ወያኔ መከላከያ ሰራዊት ለአባይ ግድብ መስሪያ ገንዘብ አናዋጣም አሉ


11144995_814272385352811_3462902730849957444_o
የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት መከላከያ
ሰራዊት ለአባይ ግድብ መስሪያ ገንዘብ እንዲያዋጡ ለቀረበላቸው ጥሪ። እንዳልተቀበሉት ምንጮቻችን ከመከላከያ ውስጥ ገለፁ፣በምንጮቻችን መረጃ መሰረት።- የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንደ አዲስ ለአባይ ግድብ መስሪያ የሚሆን በሚል ገንዘብ እንዲያዋጡ በአመራሮቻቸው ለቀረበላቸው ጥሪ። አንቀበልም ማለታቸውን የገለፀው መረጃው። ለቀረበው ጥሪ ሳይቀበሉት የቀሩበት ምክንያትም “ ባለፉት ጊዚያት በተደጋጋሚ የከፈልነውን ገንዘብ ቦንድ ይሰጣቸኋል ተብለን እስከ አሁን ድረስ ግን ሳይተገበር አንከፍልም” እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፣
መረጃው በማከል።- የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች በሰራዊቱ ውስጥ አጋጥሞ ያለውን ለአባይ ግድብ ገንዘብ አንከፍልም የማለቱ የመበታተን አደጋ። እንዴት አድርገን ለሰራዊቱ እናሳምነው በሚል በከባድ ውጥረት እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል

No comments:

Post a Comment