Monday, September 21, 2015

በጋምቤላው ግጭት 126 ሰዎች መገደላቸውን መንግስት ገለጸ

መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቃቢ ህግ ለፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ ቀድም ብሎ 60 ሰዎች መገደላቸውን ከጠቀሰ በሁዋላ፣ አሻሽሎ ባቀረበው ክስ 126 ሰዎች በወረዳ አመራሮች ትእዛዝ መገደላቸውን ጠቅሷል።

በማዣንግ፣ ጎደሬና ሚጤ በሃላፊነት ላይ የነበሩ የወረዳ አመራሮች ” ደገኞች ቦታችንን ለቀው ይውጡ፣ ደገኞች በማዣንግ ዞን ውስጥ የያዙትን የእርሻና የቡና ተክል መሬት ለማዣንግ ብሄር ተወላጆች ያካፍሉ” የሚል ንግግር መድረጋቸውንና በዚህም ሳቢያ ግጭት መቀስቀሳቸውን ይዘረዝራል።
ደገኞች እየተባሉ የሚጠሩት የሌሎች አካባቢ ተወላጆች ቡናችንንና አትክልቶቻችንን አናካፍልም በማለታቸው የፖሊስ አባላትና ሚሊሺያዎች እርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ ማስተላለፋቸው በክሱ ላይ ተመልክቷል። ባለስልጣናቱ ብሄረሰቡን መሳሪያ በማስታጠቅ እርምጃ እንዲወሰድ በሰጡት ትእዛዝ ፣ ለአንድ አመት ያክል ደም አፋሳሽ ግጭት ተከስቷል። ግጭቱን ተከትሎ ከ7 ሺ ያላነሱ ሰዎች ተፈናቅለዋል።
መኢአድ በወቅቱ ከ600 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ጠቅሶ ነበር። የአካባቢው ተወላጆች በበኩላቸው የቀድሞ የህወሃት ታጋዮችና ወታደራዊ መኮንኖች የአካባቢውን መሬት መቀራመታቸው ለግጭቱ መነሳት መንስኤ ነው ይላሉ።

No comments:

Post a Comment